Wednesday, August 15, 2012

ኩክ የለሽ ማርያም ተከሰተ የተባለው ፍንዳታ ከእውነት የራቀ ነው


  • የገዳሙ አስጎብኚ ዲያቆን ሃይለማርያም ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ደውለን ምንም አይነት ፍንዳታ እንዳልነበረ ጠቅሰው ምዕመናኑ በተሳሳተ መረጃ እንዳይደናገጡ አስታውቀዋል ፤ 

  • የዲያቆን ሃይለማርያም ስልክ 0912162878

(አንድ አድርገን ነሐሴ 9 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- ዛሬ ጠዋት ዘሀበሻ የተባለው  ድረ-ገጽ ላይ እንዲህ የሚል መረጃ ወጥቶ ነበር
“ደብረብርሃን ከተማ አካባቢ በተለምዶ ኩክ የለሽ ማርያም ተብሎ በሚጠራው ቤ/ክ አካባቢ ምንነቱ ባልታወቀ ፍንዳታ ለሱባዔ የገቡ ምዕመናን ሞቱ፤ በርከት ያሉ ሰዎችም እንደቆሰሉ የምንጮቻችን ዘገባ አመለከተ። ምንጮቻችን በኩክ የለሽ ማርያም አካባቢ የፈነዳውን ማን እንዳጠመደው እንዳልታወቀ ገልጸው፤ የሞቱት ሰዎች ቁጥርም እስካሁን እየተጣራ መሆኑም፤ የቆሰሉትም በርካታ እንደሆነ እንጂ ቁጥሩ ለጊዜው እንደማይታወቅ ገልጸዋል። የ16 የኪነምህረትን ጾም በማስመልከት በኩክ የለሽ ማርያም ቤ/ክ በርከት ያሉ ምዕምናን ከተለያዩ ቦታዎች በመጓዝ ሱባዔ የሚገቡ ሲሆን ይህ አደጋ መከሰቱ እጅጉን አነጋግሯል፤ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች መንግስት ራሱ አፈንድቶ ከሙስሊሞች እንቅስቃሴ ጋር ለማያያዝ ያደረገው ሴራ ሊሆን ይችላል እያሉ ነው።” በማለት  በመረጃ ያልተደገፈን ዜና አስነብቦናል፡፡


ነገር ግን እኛም ይህን ጽሁፍ ካነበብን በኋላ ጊዜ ሳንወስድ ኩክ የለሽ ለሱባኤ የሄዱ ሰዎች ጋር ደውለን ማረጋገጥ እንደቻልነው ፤ በቦታው ምንም የተከሰተ ነገር የለም ፤ ምዕመኑ በሰላም ጸሎቱን እያደረሰ መሆኑን ለማረጋገጥ ችለናል ፤ የፈነዳ ቦምብም የተባለውም እንዳልተፈጠረ ነግረውናል ፤ ባይሆን ይህን የመሰለ ችግር በእነዋሪ አርሴማ ገዳም እንደተከሰተ ለማወቅ ችለናል ፤  አንድ ቆለኛ የፈጠረው ችግር እንጂ መንግስትንና ከአክራሪ ሙስሊሞች ጋር የሚያያይዘው አንዳች ነገር አለመኖሩን ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል ፤ የሆነው የተደረገውን ነገር ከደብረ-ብርሐን ከተማ ወደ ቦታውም ያመሩ ሰዎች ስላሉ  ሲመለሱ ሁኔታውን አጣርተን መረጃው ሲደርሰን እናቀርባለን ፤ 

No comments:

Post a Comment