Thursday, August 16, 2012

እውነት ነው አቡነ ጳውሎስ አርፈዋል




(አንድ አድርገን ነሐሴ 10 2004 ዓ.ም)፡- የአቡነ ጳውሎስ ማረፍ እውነት ሆኗል ፤ አሁን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ሸገር ሬዲዮ እንደገለጸው ከሆነ ከቤተክህነት ባገኝው መረጃ መሰረት የአቡነ ጳውሎስ በ76 ዓመታቸው ማረፋቸውን ተናግሯል ፤ ብጹአን አባቶች በስብሰባ ላይ መሆናቸውንም ገልጧል ፤ መንበረ ፓትርያርክ ውስጥ ያሉ ሰራተኞች ሁሉም እያነቡ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል ፤ከሲኖዶስ ጽህፈት ቤት ትክክለኛ መረጃ ለሸገር ሬዲዮ አስተላልፈዋል ፤ በርካታ የሃይማኖት አባቶች ሀዘን ላይ ናቸው ፤ አስከሬናቸው በባልቻ ሆስፒታል መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል ፤ ቀጣይ የቀብር ክንውን የሲኖዶስ መግለጫ ይጠበቃል፡፡

ነፍሳቸውን በገነት ያሳርፍልን

እውነት ነው አቡነ ጳውሎስ አርፈዋል

1 comment:

  1. ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የኢትዮጵያ ፓትሪያሊክ ከዚህ አለም በሞት በስጋ በመለየታቸው እጅግ በጣም አዝነናል። ሆኖም ግን እውነተኛ
    የጌታ ሐዋርያ ፣ የሐይማኖታችን አርበኛ፣ በትእግስት የሚገባውን ሩጫ ፈፅሞ ወደ ጌታው በመሄዱ ደግሞ ፍፁም ክርስቲያናዊ ደስታና ሃሴት
    ተሰምቶናል። ሰው የማያውቀውን የድል አክሊል የሚያውቀው አምላኩ እግዚአብሔር እንደሚያቀዳጀውም በምሥሉ ልብ እናምናለን።

    እኛም ክርስቲያኖች ከብፁእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ፤ ፈተናንና መከራን በትእግስት ማሳለፍን ተምረናል። እግዚአብሔር አምላካችን ከቅዱስነታቸው ረድኤትና በረከት ያካፍለን እንላለን፣ አሜን፣ አሜን፣ አሜን።

    ReplyDelete