Saturday, August 18, 2012

በቅድሰት አርሴማ ተከሰተው የተባለው አደጋ


(አንድ አድርገን ነሐሴ 12 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- ከ3 ቀናት በፊት ዘሀበሻ የሚባል ድረ ገጽ በደብረብርሃን የምትገኝው ኩክ የለሽ ገዳም ቦምብ መፈንዳቱን እና በፍንዳታውም ሶስት ሰዎች እንደሞቱ ፤ የሟ ቁጥርም እንደሚጨምርና በርካቶች እንደቆሰሉ አስነብቦን ነበር ፤ ይህንም ነገር ከሙስሊሞች እና ከመንግስት ጋር አያይዞ አስቀምጦ ለመመልከት ችለናል ፤ እኛም ጉዳዩን በሰማንበት ጊዜ የገዳሙ አስጎብኚ ጋር ስልክ በመደወል ስለተባለው ነገር ጠይቀን እንዳረጋገጥነው “ይህ በሬ ወለደ ወሬ ነው እኛ ጋር ምንም የሆነ ነገር የለም” በማለት አለመከሰቱን አረጋግጠውልናል ፤ ከዚህም በተጨማሪ ምዕመኑ በወፍ ዘራሽ ወሬ እንዳይረበሽ መልዕክታቸውን አስተላልፈውልን ነበር ፤ ምዕመኑ በስልክ በቀጥታ ደውሎ እንዲያረጋግጥም ስልክ ማስቀመጣችን ይታወቃል ፤ ይህን በዚህ ከቋጨን በኋላ ሰንቀታ አርሴማ ችግር መፈጠሩን መረጃ ከደረሰን በኋም ጉዳዩንም ለማጣራት ሰዎች ወደ ቦታው እንደሄዱና ሲመለሱ መረጃውን እንደምናቀርብ ቃል መግባታችን ይታወቃል፡፡ 


ሰንቀታ አርሴማ ገዳም  ከአዲስ አበባ ደብረ ብርሃን 130 ኪሎ ሜትር ከሄዱ በኋላ ከደብረብርሃን ደነባ ፤ ከደነባ እስከ ሲያ ደብር ድረስ የ6 ብር የትራንስፖርት መንገድ ሄደው በእግር የ 1፡30 መንገድ ተጉዘው ሲያበቁ  በሰንቀታ ገበሬ ቀበሌ ማህበር ውስጥ ቅድስት አርሴማን ያገኟታል ፡ በቦታው የተፈጠረው ነገር ዘሀበሻ ድረ-ገጽ እንዳለው ከአክራሪ ሙስሊሞች እና ከመንግስት ጋር እንደማይገናኝ ቦታው ድረስ ከሄዱ ሰዎች ለማረጋገጥ ችለናል ፤ ጊዜው የሱባኤ ወቅት እንደመሆኑ መጠን አርሴማ በርካታ ምዕመናን ከአዲስ አበባ እና ከደብረብርሀን ከተማ ተነስተው 16ቱን ቀናት የሚያሳልፉበት ልዩ ቦታ ናት ፤ በጊዜው ቦምቡ ሊፈነዳ የቻለው የአእምሮ እና የመንፈስ ችግር ባለበት አንድ ለጸበል በመጣ ሰው መሆኑ ለማወቅ ተችሏል ፤ ያፈነዳው ሰው በቦታው የነበሩ ጸበልተኞች እንደመሰከሩት ለጸበል የመጣ ችግር ያለበት ሰው መሆኑን ተናግረዋል ፤ በፍንዳታው 2 ሰዎች ሲሞቱ 3 ሰዎች ደግሞ ቀላልና ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል ፤ ፖሊስ  ወደ ቦታው አምርቶ ይህን ነገር የፈጸመውን ሰው በቁጥጥር ስር ሊያውል ችሏል ፤ ይህ ሰው ቦምብን ያህል ነገር ለምን ወደ ጸበል ቦታ ድረስ ይዞ እንደመጣ ሌላ ጥያቄ ፈጥሯል ? ነገር ግን የአካባቢው ፖሊስ ይህ ሰው በቁጥጥር ስር ቢያውለውም የአእምሮ እና ከመንፈስ ጋር በተያያዘ ችግር ለጸበል የመጣ ሰው በመሆኑ ፖሊስ የሚጠይቀውን ጥያቄ በአግባቡ መመለስ የማይችል ከመሆኑ ባሻገር ጉዳዩን በአግባቡ ማጣራት አልቻለም ፤ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች እና ቦምቡን ያፈነዳው ሰው በደብረ-ብርሃን ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል ፤ ቦምቡን አፈንድቷል የተባለውን ጸበልተኛ በሁለት ፖሊሶች እየተጠበቀ የእምሮ በሽታውን በሆስፒታል ሆኖ ህክምናውን እየተከታተለ ይገኛል፡፡

አሁንም ደግመን መናገር የምንፈልገው ይህ አደጋ በሽብርተኞች ወይንም ዘሀበሻ ድረ-ገጽ እንዳለው በመንግስት አልተከሰተም ፤ መንግስት ይህን ያህል ቦታ ተጉዞ ህዝብ ላይ ሽብር ይፈጥራል የሚል ግምት የለንም ፤  ጉዳዩንም አሁን ከሚነፍሰው ንፋስ ጋር ማያያዙ ተገቢ አይመስለንም ፤ እኛ የምንናገረው እንደ ዘሀበሻ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኝት አይደለም ፤ በቦታው የሆነውን የተደረገውን ነገር ብቻ እንዘግባለን ፤ ይህን የመሰለ የሽብር ወሬ በሌላ ገዳምም ተከሰተ ተብሎ ለጥቂት ሰዓታት ምዕመናን መረበሻቸውን ሱባኤ ላይ ያሉ ሰዎች በርካታ ስልኮችን ከቤተሰቦቻቸውና ከጓደኞቻው እንዳስተናገዱ ለማወቅ ችለናል ፤ ይህን አይነት ወሬ ለሱባኤ ገዳም የሄደን ሰውን ሆነ ቤተሰብን እንደሚረብሽ ይታወቃል ፤ ስለዚህ ነገሮችን ሳናረጋግጥ በኤሌክትሮኖክ ሚዲያዎች ላይ የሚተላለፉ ወሬዎችን ማመን መቻል የለብንም የሚል አስተያየት አለን ፤  ማን ያውቃል ይህን የመሰለ ሽብር በመንዛት ምዕመኑን ሰላም ሊነሱ የተደራጁ አካላት አለመኖራቸውን ? በተከሰተው ነገር በጣሙን አዝነናል ለሟች ቤተሰቦች መጽናናቱን እግዚአብሔር ያድላቸው፡፡ 

ቸር ሰንብቱ

4 comments:

  1. Something not right with this report. How do you know a guy who blast a bomb in "Tsebe" area his own agenda? I don't think mentally challenged personal able to find Bomb at first place. even if he had bomb it's unlikely mentally challange person to plan things. This guys took bomb with him to "Tsebel" and blast there. It's plan for me. Are you guys trying to cover up???

    ReplyDelete
  2. Dear Andadrgen

    You are the eyes and ears of our tewahedo church.
    Excellent up to date informatiom.

    May GOD bless u all

    ReplyDelete
  3. i donot think this person is mentally sick. Planning and puting the bomb properly needs high level skills and focus. I am not convinced with what you indicated above. In the first place a sick person (mentally) donot able to think properly, let alone puting bombs.
    regards

    ReplyDelete
  4. How can a mentally sick person plan and carries a bomb to a holiest place? Where did he found it? How does he operate it? How colud he be safe from explosion if mentally abnormal? Be logical in reporting such issues.

    ReplyDelete