Thursday, August 2, 2012

ኦርቶዶክሳውያን ድረ-ገጾችን ለማዘጋት እየተዶለተላቸው ይገኛል


(አንድ አድርገን ሐምሌ 25 ፤ 2005 ዓ.ም)፡- ዘመኑን ዋጁ እንዲል ቃሉ ከጊዜ ወዲህ ድረ-ገፆች መረጃን ለምዕመናን እያስተላለፉ ይገኛሉ ፤ የአምስት ዓመት እድሜ ያስቆጠረችው በእድሜ አንጋፋዋ “ደጀ ሰላም”ን ጨምሮ ፤ አንድ ዓመት በቅጡ ያልሞላት “አንድ አድርገን” ፤ ደቂቀ ናቡቴና አሐቲ ተዋህዶን የመሰሉ ገጾች የቤተክርስትያንን መረጃዎች የመናፍቃንን አካሄዶች በየጊዜው በማውጣት ይታወቃሉ ፤ ከዚህ በተቃራኒ በሌላኛው ጎራ የቆሙ የተሀድሶያውያን እና የመናፍቃን ገጾች ያለመታከት ቤተክርስትያኒቱን ለመከፋል ያለ እረፍት እየሰሩ ይገኛሉ ፤ “አባ ሰላማ”ና አውደ ምህረትን የመሰሉት ገጾች ውስጥ በሚገኙ እነሱን ከሚመስሏቸው ሰዎች ጋር በመሆን መረጃዎችን እየተቀባበሉ ምንፍቅናቸውን እና ኢ-ኦርቶዶክሳዊ የሆነ አካሄዳቸውን በጽሁፋቸው እየገለጹ ይገኛሉ ፤ የነዚህን ገጾች ጽሁፍ አይቶ እነ ማን እንደሆኑ ለማወቅ የተለየ ብልሀትን የጠለቀ ምርመራ ማድረግን አይጠይቅም ፤ ቅዱሳንን የሚዘልፉና  ገድላትን የሚያንቋሽሹ ጽሁፎቻቸው ምስክሮቻቸው ናቸው፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ ደጀ-ሰላም እና አንድ አድርገን በኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይነበቡ ቢደረግም እነዚህን የመሰሉ የተሃድሶያውያን ገጾችን ግን የደረሰባቸው የለም ፤ አሁን ደግሞ ይባስ ብሎ ከወደ አሜሪካ እነዚህን ገጾች እንዲታገዱ የሚጠይቅ ስብሰባ መደረጉን የአቋም መግለጫ መውጣቱን የሚያመላቱ መረጃዎች ወጥተዋል ፤ ከበስተጀር እየተዶለተላቸው ይገኛል ፤ እነርሱ አልገባቸውም እንጂ “አንድ አድርገን” እና “ደጀ ሰላም” በፌስ ቡክ ካልሆነ በስተቀር በቀጥታ የማይነበቡበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል ፤ አንድ አድርገን በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ አሁን ለ3ተኛ ጊዜ እክል ገጥሟታል ፤ ከዚህ በፊት አንድ በአንድ እየተባለ ሁለት ገጾች ቢዘጉም አሁን ግን በተለዋጭነት መረጃ ለማስተላለፍ የምትተቀምባቸው 6 ገጾች በጠቅላላ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይሰሩ ተደርገዋል ፤ ይህ ሁሉ ቢሆንም ከኢትዮጵያ ውጭ በቀን ቢያንስ በሺህ በሚቆጠሩ ሰዎች እንደምትጎበኝ የብሎጉ ስታተስ ይጠቁማል ፤ ከቀናት በኋላም እነርሱ መዝጋት ካልሰለቻቸው እኛ መክፈቱ ስለማይከብደን ተጨማሪ አማራጭ ገጾች እንደምንከፍት በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡


እንደ “አንድ አድርገን” እምነት ካለው ተጨባጭ ሁኔታ በመነሳት የተሃድሶያውያን እና የመናፍቃንን አካሄድ መረጃዎች ሰዎች ዘንድ አድርሰናል ብለን አናምንም ፤ እስከ አሁን ካወጣው መረጃ እየሰበሰብንና እያጠናከር ያሉ ጉዳዮች ይበዛሉ ፤ የሐዋሳው ጉዳይ ዳግም ለመቀስቀስና ምዕመኑን ወደማያባራ ቀውስ ውስጥ ለመክተት በማሴር እነ ያሬድ አደመ ስራቸውን እየሰሩ ይገኛሉ ፤ ቅዳሴ ቤተክርስቲያን እያስቀደሱ ወንጌሉን ደግሞ በአዳራሽ የሚል ፈሊጥ በመያዝ ለተግባራዊነቱ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ ፤ ውስጦቻችን ተሰግስገው ያሉ አመቺ ጊዜ የሚጠብቁ ሰዎች ተበራክተዋል ፤ አሁንም በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን እና መናፍቃኑ አዳራሽ የሚመላለሱ ሁለቱም ጋር የሚያገለግሉ ሰዎች ተበራክተዋል ፤ በተመሳሳይ አንዳንድ ከተማዎች ላይ የቅባት እና የጸጋ አስተምህሮ ያላቸው ሰዎች ምዕመኑን እያመሱት ይገኛሉ ፤ ከነዚህ በተጨማሪም አሁን የማናመላክተው  በርካታ ነገሮችም አሉ ፤ እነዚህ ሁሉ ጉዳዮች ወደፊት ጊዜውን ጠብቀው የሚፈነዱ ቦምቦች ናቸው ፡፡

ስለዚህ ማንም የድብቅ ሸንጎ በመጥራት እኛ ላይ ብሎጋችንን ለማዘጋት ቢያሴሩ ፤ ከቤተክህነት በቀጥታ ለመንግስት ብሎጎቹ እንዲዘጉ ደብዳቤ ቢጻፍ ፤ መንግስትም ከራሱ ፍላጎት በመነሳት በሌላ አይን በመመልከት ብሎጋችንን ቢዘጋ ፤ እኛ ግን ከመጻፍ ወደ ኋላ የሚገታን አንዳች ነገር አይኖርም ፤ እነርሱ ለመዝጋት ካልደከማቸው እኛ አዲስ ለመክፈት አይሰለቸንም ፤ አፍራሽ ግብረ ሃይሎችን አይተን ዝም የምንልበት አይን ሰምተን ጆሮ ዳባ ልበስ ብለን የምናልፍበት ጆሮ የለንም ፤  ጽሁፎቻችን ዋልድባ ከሚገኙ መነኮሳት ጀምሮ በተለያዩ ሀገሮች ድረስ ተደራሽ መሆን ችሏል ፤ ቀድሞ በቀን ከ5ሺህ ሰዎች በላይ ቢጎበኙንም አሁን ብሎጉ ተዘግቶ ቢያንስ በቀን መረጃውን ከ3ሺህ በላይ ሰዎች ጋር ስለምናደርስ ተስፋ ባለመቁረጥ እንሰራለን፡፡
ተጨማሪ ሁለት ገጾችን ኢትዮጵያ ውስጥ ለመነበብ እንሞክራለን


ቸር ሰንብቱ 

6 comments:

  1. Wow Andadrgen , we are very proud of you guys,May GOD bless u all. GOD is with us we will prevail.
    ስለዚህ ማንም የድብቅ ሸንጎ በመጥራት እኛ ላይ ብሎጋችንን ለማዘጋት ቢያሴሩ ፤ ከቤተክህነት በቀጥታ ለመንግስት ብሎጎቹ እንዲዘጉ ደብዳቤ ቢጻፍ ፤ መንግስትም ከራሱ ፍላጎት በመነሳት በሌላ አይን በመመልከት ብሎጋችንን ቢዘጋ ፤ እኛ ግን ከመጻፍ ወደ ኋላ የሚገታን አንዳች ነገር አይኖርም ፤ እነርሱ ለመዝጋት ካልደከማቸው እኛ አዲስ ለመክፈት አይሰለቸንም ፤ አፍራሽ ግብረ ሃይሎችን አይተን ዝም የምንልበት አይን ሰምተን ጆሮ ዳባ ልበስ ብለን የምናልፍበት ጆሮ የለንም ፤ ጽሁፎቻችን ዋልድባ ከሚገኙ መነኮሳት ጀምሮ በተለያዩ ሀገሮች ድረስ ተደራሽ መሆን ችሏል ፤ ቀድሞ በቀን ከ5ሺህ ሰዎች በላይ ቢጎበኙንም አሁን ብሎጉ ተዘግቶ ቢያንስ በቀን መረጃውን ከ3ሺህ በላይ ሰዎች ጋር ስለምናደርስ ተስፋ ባለመቁረጥ እንሰራለን፡፡

    ReplyDelete
  2. weye medehaniyaleme mene yeshalale?

    ReplyDelete
  3. Wondimoche ena ehitoche Ayzoachihu, Ke'ashenafiwoch hulu yemibeltew yeqidusan amlak kenante gar new. Hodachew amlakachew kibrachew benewurachew yehonebachew wegenoch le gibir abatachew lediabilos mesariya honewu binesum kegna gar yalut kenesu gar kalut yibeltaluna wedhuwala atbelu.

    Patriarchum honu bediyaspora yalut ' kahinat tebiye" yegibir tebabariwoch yegil biltsiginachew enji mahiberat lebete kirstiyetean yemiserut melkam sira ayasdesitachewum. Filagotachew yaleminim kelkay mezref new.

    Wugiyawu eske elete mtsi'at deres yiqtilal. Ayzoachihu. Egziabher kehulachin gar yihun.

    ReplyDelete
  4. "የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ" ውድ የአንድ አድርገን አዘጋጆች የገጠማችሁት ከዘርፈ ብዙ ጠላት መሆኑን አትዘንጉ፣ ጠላት ያለ የሌለ ቀስቱን በቤተ ክርስቲያን ላይ እየወረወረ ነው የቤተ ክርስቲያን ልጆች ደግሞ እናታችን አለንልሽ ማለታቸው ከቀስታቸው ማለቅ ጋ ተደማምሮ ጭንቀት ውስጥ ጥሏቸዋል:: በክህደት በጎጠኝነት በዘራፊነት በአድርባይነት በግደለችነት እና በቸልባይነት ሁሉም ተሰልፈውባታል:: ይሁን እንጅ ያለጠባቂ የማይተወን አምላክ ብዙዎችን ካንቀላፉበት ወደ ንቃት እንድሁም ወደዝግጁነት አድርሷቸዋል:: እናም በሱ መመካታችን ይህ ነው:: እነዚህ ከበጣም ክፉ ክፉ ይሻላል ብለን ያከበርናቸው በባለስልጣን ዘመናቸው በጉቦ የናወዙ የብዙ ደሃ ገንዘብ የዘረፉ የሙዳየ ምጽዋት መቀመጫዎችን ያራቆቱ አሁንም የቀራቸውን ዘረፈው ሊያዘርፉን ደፋ ቀና ማለታቸውን እንደቀላል የምናየው መስሏቸዋል:: ለመሆኑ በሚኖሩበት አሜሪካ ሃሳብን በነጻነት መግለጽ የነጻነታቸው መርህ እንደሆነ ረስተውታል:: ለነገሩ በሰለጠነው አገር ይኖራሉ እንጅ የሚያስቡት የመጡበትን ጎስና ነገድ ብቻ እንደሆነ በያለንበት ቦታ እናውቀዋለን:: አብረናቸው ይህን ያህል ዘመን ስንቆይ ስንትና ስንት የሚያከባብሩ ነገሮችን አብረናቸው አድርገን እስከአሁን ፍቅር የለንም:: አለመታደል ነ ው እንጅ ምን ይባላል:: ለመንኛውም በቁጥርም በይዘትም እንደምንበልጣቸው አላወቁም:: በአገራችንም የነጻነት ጭላንጭል በርቀት እየታየ ነው እኩልነት እና ዳኝነት ተጠያቂነትና ኃላፊነት የሚሰማው አሰራር ከፊታችን አለ ያኔ የዘረፈም እንዳዘራረፉ ፣ ክህደት የፈጸመም እንደአፈጻጸሙ ፍርዱን የሚያገኝበትን ቀን ይጠብቅ:: የሚሻል የነበረው ግን ከአሁን በኋላ ባለው ጊዜ እንኳን ከክፋታቸው ቢመለሱ ነበር::
    እናንተ ግን አይዟችሁ እርሱ ያለጠባቂ እንዳይተወን እናምናለን::

    ReplyDelete
    Replies
    1. Egzeabher ayitewenim
      Abet yeziyan gize Kiristos simeta
      Tinishum tilikum medreshawin siyata
      egnas hulem le'Betekrstianachin le'andinetachin enitegalen enesu degimo legosa, le'genzeb ena le'shumet yitegalu lenefsachew meche yihon yemiyasibulat? yetsidikis sira sertew yemiyaserut meche yihon?

      Delete
  5. መልካም ዜና ይሁንላችሁ ኢትዮጵያ ውስጥ የእናንተ እና ሌለሎች ማኅበራዊ ድህረ ገጾች ቢዘጉም መክፈቻ ቀላል ሶፍትዌር ስላለ ለአንባቢዎቻችሁ ብቻ በኢሜል አድራሻ ማስተላለፍ ይቻላል እናንተ ግን በርቱልን በተለይ የውስጥ አርበኛ የሆኑትን ተኅድሶያውያንንና ስራዎቻቸውን ማጋለጥ አታቁሙ እኛም መረጃ ስናገኝ እናቀብላችኋለን
    እግዚአብሔር ሀገራችንና ሃይማኖታችንንና ህዝቦቿን ይጠብቅልን

    ReplyDelete