Thursday, August 30, 2012

“ኢትዮጵያ ቀኑ ጨለመባት” ተሀድሶያውያን ለአቶ መለስ ዜናዊ ያወጡት መዝሙር


መጀመሪያ ይህን መዝሙር ያድምጡ  Click here
 
(አንድ አድርገን ነሐሴ 24 2004 ዓ.ም)፡- ተሀድሶያውያን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሞት ምክንያት በማድረግ “ኢትዮጵያ ቀኑ ጨለመባት” የሚል መዝሙር በማውጣት ለመንግስት እንደ ገጸበረከት አቅርበዋል ፤  ጥቂት የተሀድሶያውያን አቀንቃኞች አቡነ ጳውሎስ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ ቀኑ ጨልሞባቸው ሊሆን ይችላል ፤ ከአሁን በኋላ በማን አማካኝነት ሲኖዶሱንና ህዝበ ክርስትያኑ መሀል ገብተው የሚበጠብጡበት በራፉ ተዘግቶባቸውም ይሆናል ፤  ነገን ሲያስቡት ጨልሞባቸው ሊሆን ይችላል ፤ ቤተክርስትያን ግን ምዕመኑን እንዲያገለግል የሾመችው ፓትርያርክ አባት በህይወት ቢኖሩም በሞት ቢለዩም ቀኖች  አይጨልሙባትም ፤ ይህ መዝሙር ቤተክርስቲያንን ወክሎ በኦሮሚያ ቴሌቪዥን ሲተላለፍ ነበር ፤ ይህ በጣም አሳፋሪ ተግባር ነው ፤ ግጥሙ ዜማው ሳይመረመር ስለወጣ ብቻ በቴሌቪዥን ማቅረቡ ትክክል አይደለም ፤ ሰዎቹ ምንፍቅናቸውን ቤተክርስትያኒቱ ላይ ለመጫን ስርዓቷን ለመበረዝ ወደፊት ይመረጣሉ ተብለው የሚጠበቁት አባትን ሲያስቧቸው ሊጨልምባቸው ይችላል ፤ ኢትዮጵያም ብትሆን አንድ መሪ ስለሞተ ጨለመባት ማለት አግባብ አይደለም ፤ ማንም በዚች ምድር ላይ ቋሚ የለም ፤ ሁሉም ጊዜው ሲደርስ ይሸኛል ፤ ዓለም ኮንትራት ነች ፤ በእግዚአብሔር የሚያምን አንድ ሰው በሞት ተስፋ አይቆርጥም ሊጨልምበትም አይገባል ፤ የሚያኖረን የዓለም ብርሀን መድኃኒዓለም ነው፡፡ እኛ ወደፊት ብርሀን ይታየናል ፤ ለጥቅማቸው በቤተክህነቱ ዙሪያ የተሰገሰጉ ተሀድሶያውያን ደግሞ ነገ ጨለማ ሊታያቸው ይችላል ፤ ብርሃናቸውን ተነጥቀዋልና ፤ እንደ ከዚህ በፊቱ ተጽህኖ ፈጣሪ የሆነ አባት ለማግኝት የሚከብድ ስለሚሆንባቸው ጨለማው ይበልጥ ገዝፎና ከብዶ ታይቷቸው ይሆናል፡፡ 
እውን ቀኑ ለኢትዮጵያ ጨልሟል? ወይስ ጨለማው የሚገፈፍበት ቀኑ ደርሷል ? እስከ አሁን በብርሀን እንደኖርን የሚነግረን ሳይኖር ኢትዮጵያ ቀኑ ጨለመባት ይሉናል ፤ ጨለማ ከብርሀን በኋላ የሚመጣ ነው ፤ ብርሀን ደግሞ ከጨለማ በኋላ ፤ አሁን እሆነ ያለው የቱ ነው የሆነው ? ከብርሀን ወደ ጨለማ ? ከጨለማ ወደ ብርሀን ? ወይስ ከጨለማ ወደ ድቅድቅ ጨለማ ? ከጊዜ በኋላ አንዱ ይሆናል ፤ አሁን ግን ምንም የጨለመ ነገር የለም ፡፡ ለቤተክርስትያን ባለፉት 20 ዓመታት ጨለማ ናቸው ባንልም ብርሃን ነው ማለት አንችልም ፤ ነገንም አናውቅም ተስፋችን ግን በብርሀን መመላለስ ነው ፤  ለማንኛውም መንግስትን ለማስደሰት ሲባል የቤተክርስትያኒቱን ስርዓት መናድ ተገቢ አይደለም ፤ 

21 comments:

  1. አንድ ነገር አስታወሰኝ:: ከዚህ በፊት እነዚህ ሰዎች የምንፍቅና ሥራ ነው የሚሠሩት በሚል እዚህ "አንድ አድርገን" ላይና "ደጀሰላም" ላይ በተደጋጋሚ ሲተቹ እሰማለሁ አያለሁ:: አብዛኛውን በአርምሞ ነበር የምከታተለው::

    አሁን ግን ቅጥ አጣ! ሰዎቹ ቀጥታ ሰው እያመለኩ እንደሆነ ታየኝ:: መጀመሪያ "መዝሙሩን" ሳይ በራሴ የፌስቡክ ገጽ ላይ ስሜቴን ገልጬ እስቲ "አንድ አድርገን" ወይም "ደጀሰላም" አይተውት ከሆነ ምን ብለው ይሆን ብዬ ጎራ አልኩ:: እናንተ ጽፋችሁ ሳይ አስተያየተን ለመስጠት ደፈርኩ:: በእንጭጯ ዕውቀቴ የእግዚአብሔር ቃልን ተንተርሼ በራሴ ገጽ ላይ የለጠፍኳትን ለእናንተ እንደሚከተለው ላካፍል::

    "ኢትዮጵያ ቀኑ ጨለመባት" ምን ማለት ነው? መጽሐፉ ደግሞ የሚለው "ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች (መዝ 88 ፥31)":: እጆቿን ወደ እግዚአብሔር የምትዘረጋ ሀገር ደግሞ አይጨልምባትም:: ይህ ቃል ጊዜ የማይገድበው በእኛ በሰዎች አዕምሮም የሚወሰን አይደለም:: ይህ ቃል ዛሬ በሞተ-ሥጋ ከተለዩን ሰዎች በፊትም የነበረ: ዛሬም ያለ: ወደፊትም የሚኖር ነው::

    ይህንን "መዝሙር" የቃረበ ሰው እግዚአብሔርን ወይስ ግለሰቦችን ሲያመልክ ነበር? የምናመልከው አምላክን ነው ወይስ ግለሰቦችን? መዝሙርስ ትርጉሙ ምንድነው? ስለ ደግ ሥራቸው እግዚአብሔር ያስባቸው: ስለ ጥፋታቸው ይቅር ይበላቸው ብሎ መመኘት እያለ እነርሱን ወደ ማምለክ መሄድ ግን የአምላክ ትዕዛዙን መሻር ይሆናል:: እንዲህም ይላል " ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ:: (ዘጸ 20 ፥ 3)"
    ". . . እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና::(ዘጸ 20፥ 6)"

    እውነት የኢትዮጵያው የዜማ አባት (ቅዱስ ያሬድ) እንደዚህ በአንድ ምሽት እንዳልደረሰ ያውቁ ይሆን እነዚህ ሰዎች? ቴዲ አፍሮ ቀነኒሳ ሃይሌን ወደኋላ ዙሮ እያየ ሲሮጥ አይቶ የተሰማውን ባንድ ምሽት ሰርቶ ሲያሳየን ከሀገር ፍቅር የተነሳ አብረን ተደስተንበት አይተናል:: ይሄኛውም እንደዚያ ዓይነት መስሏቸው ከሆነ ኧረ ሊታረሙ ይገባል? ኧረ የኃይማኖት ጉዳይ ነው? ኧረ የተዋሕዶ ጉዳይ ነው? ኧረ አንብበን ዝም አንበል?

    ReplyDelete
    Replies
    1. Egziabher yisteh le ezih asteyayeteh enem yanten tsihuf copy aderege FB eletifewalehu....thanks

      Delete
  2. አንተ ነፍሰ ገዳይ የነፍሰ ገዳይ ልጅ።ምቀኛ አነተእና የዲያብሎስ ማህበር መቃብር ውስጥ ካልከተትነው ታያለህ በዚያንን ጊዜ ሰው ሳይሆን ሰይጣን ይዘምርልሃል።

    ReplyDelete
    Replies
    1. ምኑ ነው የሚያስመቀኘው ? ለማሽቃበጥ መች ሰው ተመረጠና ችግር ተፈጠረ ፡፡ ከተፈለገ ራኘ ይዘጋጅላቸዋል ፡፡ የመዝሙሩ ዳር ዳሩ ቀለበት ለመጠላለቅ እየተነጠፋችሁ እንደሆነ ያስረዳናል ፡፡ ኢህአዴግ ግን ሸንኮራ አገዳ በሊታ ነው ፡፡ አካሄዱን ያውቅበታል ፤ ብልጥ ለብልጥ ሆናችሁ ፣ ፍጻሜአችሁ ከጠቀስከው ከዲያቢሎስ እንዳይሆን ለራስህ ፍራ ፡፡ የእዝን ንፍሮ ቃራሚ ፤ ቢተራርፍ ብለህ ማጐብደድህ ነው ፡፡

      Delete
  3. Who is the singer? If they are tehadiso why do u care? But you guys call orthodoxawiyan tehadiso. This is bad for the church.

    Try to think in broaden term to respect the brothers and enable people to wait in the umbrella of the church. One aspect of goodness for Aba Paulos was he was his respect to all the followers and his motive to keep all in the church.

    ReplyDelete
    Replies
    1. I don't agree with you b/c eventhough they are tehadiso they should care. Do you know why, look what he was wearing something similar to our theology graduates and also it was aired on the TV as it was orthodox Tewahedo church's song, which is not right. We Orthodox Christians don't say Ethiopia chelemebat just b/c the leaders are dead. No one is immortal we all will die. Anyways if they are tehadeso why did they say Ethiopia chelemebat b/c Abune Paulos is dead. Imagine we would't sing if one of the muslim leaders or catholic leaders died. That is the problem. I hope you will understand what I mean.

      Delete
  4. ጨለማን እንዲሁም ሀዘንን አጥብቃችሁ ተመኝታችኋልና የጠየቁትን እማይረሣ የለመኑትን እማይነሣ አምላክ አብዝቶ ይሥጣችሁ!!!

    ReplyDelete
  5. It is just for the sake of to be embraced by the government officials. Because no aba Paulos anymore.

    ReplyDelete
  6. Habtamu ahun ante belw zemare awkhalehug D/b Eprem swk chat yemtekem antebelw zemary kenu yechelemew lante new eng lemanem aydelem ante menafek neh

    ReplyDelete
  7. ፀሃይም ብርሃኗን ከልክላ ቀኑ ከጨለመብን ፣ የቤተ መቅደሱም መጋረጃ ከሁለት ተቀደደ ፣ ምድርም ተናውጠች ፣ ዓለቶችም ተሰነጣጠቁ ፣ መቃብሮችም ተከፍተው ሙታናቸውን አስረከቡ እንባልና አንደኛውን መሲሁን አጣን ብለን እንላቀስ ፡፡ ህጻኒቷን ያለዕውቀቷና ያለአግባብ ያሰገዱ ፣ አዛውንቱንም በስተርጅና አንበርክከው ለጌቶች አቤት አቤት ያስባሉ ፣ በዚህ የሃሳዊ መሲህ ግንዛቤአቸው ፣ ሰውንም እንደ ጣዖት አምልከው ይሆን ይሆናልና እግዚአብሔር መበደላችንንና መገፋታችንን ዛሬም jዚህኛው መንገድም እንዲመለከተው አቤት እላለሁ ፡፡ እንዲህ መሲህነታቸው ከታመነበት ፣ ህዝብን አራርቃችሁ ውለዱ ከሚሉ ፣ እግዜርን አራርቀህ ግደል ቢሉት ኑሮ ፣ አንደኛውን ጠራርጐ ወስዶ ጨለመብን አያስብልብንም ነበር ፡፡ ኃያሉ ፈጣሪ ግን አማካሪ የለውምና የፈቀደውን አደረገ ፡፡

    በእርግጥ በአእምሮአችን ካለን ፣ ኢትዮጵያ ቀኑ ጨለመባት የሚያስብለው ጉዳይ ፣ ከሥርዓትና ከወግ በላይ ፣ በቁም የገደሉትን ህዝባቸውን ሞተውም አንደኛውን ሊቀብሩት ፣ ሃዘን ስለሆነ ንግድ ቤትህን ሙዚቃ ስላሰማህ አትከፍትም በማለት ከዕለት መተዳደሪያው የሻይና ዳቦ ንግድ ሲያግዱትና ሲያስሩት ፣ የዕለት ሠርቶ አዳሪውንም በተንዛዛ ሃዘን ምክንያት ጦሙን ውሎ እንዲያድር ሲያደርጉት ፣ እውነትም እያጨለሙበት ነውና ሊዘመር ይገባል ፡፡ ያለ ስሜቱ ፣ ሃዘናቸውን አሸክመው በግድ እያንጋጉ ሲያስነቡትና በባዶ ሳጥን ፊት ለፊት ሲያስጮሁት እውነትም የጨለመበት ተብሎ ቢዘመር ይስማማል ፡፡ ማች ኑረው ያላማረባቸው የጐዳና ተዳዳሪዎችና ሴተኛ አዳሪዎች አለኝታችንን ተነጥቀናል ፣ የመኖር ዋስትናችንም ጥያቄ ውስጥ ወድቆብናል ብለው ሲያለቅሱና ሲያዝኑ ሲታይ ፣ እውነትም ቀኑ ጨለመ ተብሎ ይዘመርና ያለማቅማማት አንደኛውን አምልኮ ይጀመር ፡፡ የራሳቸውን ስቃይና ህመም ከማዳመጥ ይልቅ ፣ ለመሪያቸው እንዲያለቅሱ የሆስፒታልን ልብስ እንኳን ስለሥርዓት ሳይቀይሩ እያነከሱና በጋሪ እየተገፉ ተሰልፈው ለታይታ እንዲወጡ ሲደረግ ፣ እውነትም ኢትዮጵያ ጨልሞባታልና ፣ የባሰውን እንዲያርቅ ሁሉም በአንድነት ግጥሙን ቀይረው ሊዘምሩለት ይገባል ፡፡ ለፖለቲካና ከባለሥልጣኖች ለመተዋወቂያና ለመቀራረቢያ ሲባል ሃይማኖታችንንና አምልኮአችንን አናበላሸው ፡፡ ከሰዎች ይልቅ በእግዚአብሔር እንመካ ፡፡
    የማች ወገኖችን ነፍስ በምህረቱ ወደ ቅዱሳኑ እቅፍ ይሰብስብልን

    ReplyDelete
  8. እውነተኛ ክርስትያን እንኳን ቀኑ ሊጨልምበት፤ ጨለማውም ለእርሱ ብርሃን ነው:: ብርሃን የሆነ አምላክን ይዘን እንዴት ስለ ጨለማ እንዘምራለን:: ልቦና ይስጠን!!

    ReplyDelete
  9. Betam Yemigerm new min nekachew be E/G??????

    ReplyDelete
  10. Alemn yefetere geta yesewn tenkol hasab ena sera sekend balmola geze yafersewal. Yedingle mariam lig Egziabher yimesgen

    ReplyDelete
  11. Definitely, the person who sang the "Ethiopia Chelemebat" song has someone pulling his strings from protestant / tehadiso quarters. The song is against God, against the Saints of God, against the Tewahdo Church and against out mother the Blessed Virgin Mary. How does a person such as Meles Zenawi, who not only does not believe in God but also was actively in the business of demolishing God’s landmarks, brings darkness to Ethiopia upon his death? That song is a ridiculous tehadso material.

    ReplyDelete
  12. Dear Andaadrgen tanx for your hardworking up date us for current news.

    May GOD bless u Andadregen
    Now It is time all menafikan will follow .........

    ለጥቅማቸው በቤተክህነቱ ዙሪያ የተሰገሰጉ ተሀድሶያውያን ደግሞ ነገ ጨለማ ሊታያቸው ይችላል ፤ ብርሃናቸውን ተነጥቀዋልና ፤ እንደ ከዚህ በፊቱ ተጽህኖ ፈጣሪ የሆነ አባት ለማግኝት የሚከብድ ስለሚሆንባቸው ጨለማው ይበልጥ ገዝፎና ከብዶ ታይቷቸው ይሆናል፡፡

    ReplyDelete
  13. http://www.youtube.com/watch?v=h_aX99O9vAk

    ReplyDelete
  14. Be chelema wust maletuWud birk abat ena dink meri matatachinin sigelts engy Lela aydelem bekenat Menfes kemitmotu lemin ende and yehager liigi ye enanTen dirsha atiwotum hule tichit bichA!!

    ReplyDelete
    Replies
    1. የቅናት ትርጉሙ ካልተቀየረ በስተቀር ፣ ይኸ መዝሙር ወይም የሃዘን እንጉርጉሮ ከእምነት አኳያም ሆነ ከነባራዊ ሁኔታ አንጻር ስህተት አለው ማለት የቅናት ቋንቋ አይሆንም ፡፡ ፀሃይን እግዚአብሔር ይሁን ካለበት ቀን ጀምሮ ወቅቷን ጠብቃ ታበራለች እንጅ በማንም ፍጡር ሞት ጠፍታና ተዳፍና አታውቅም ፡፡ ኢየሱስ በተሰቀለበት ሰዓት እርቃኑን ለመጋረድ ፀሃይ ብርሃኗን በመከልከሏ ጨልሞ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይጠቅሳል ፡፡ ከዛ ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ዘገባ ውጭ ፣ ይህ ክስተት ዛሬ ተፈጽሞ ከሆነ በትክክል ይገለጽና ዓለም ሁሉ ጉድ ይበል ፡፡

      ከነባራዊ ሁኔታ አንጻርም ቢሆን ቀድሞውን በምድራዊ ጉስቁልና ህይወት ውስጥ ያሉትን በድህነት በዕለት ቁርስ የሚኖሩ ወገኖችንና በዘማዊነት የሚተዳዳሩ እህቶችን ፣ አንድ ግለሰብ ስለሞተ ፣ በቃ ቀኑ ጨልሞባቸዋል ብሎ ማዜምም ስድብ ነው ፡፡ በባለሥልጣን ዙሪያ ላሉ ተጠቃሚዎች መርዶ ለመንገር ታስቦ ከሆነ ኢትዮጵያ የሚለውን መለያ ዓለም የሚረዳው ፣ የደሃ ኀብረተሰብ መኖሪያነትን ስለሆነ ፣ ጨለመባችሁ ማለት ብዙሃኑን አይመለከትምና ስህተት ነው ፡፡ አንተ ያየሃቸውን ምክንያቶች እንድንመለከትልህ ደርድራቸውና እናንብባቸው ፡፡

      Delete
  15. yebirhan amlakn lemtaamelk hagere Ehtiopia ena hzbua mechem bihon kenu aychelmbatm.enastewul gobez

    ReplyDelete

  16. I hope the light will be bright for Ethiopia after now. You will cry more than this.

    ReplyDelete
  17. Enezih pentewoch ecko liasabdun new. aytachutal yihenen sisalekeben. degmo be ETV balefew slemechachal asteyayet siset nebber yihew alagach

    http://www.youtube.com/watch?v=BcEiCRj1PY8&feature=related

    ReplyDelete