Thursday, August 23, 2012

ተፈጸመ

የመጨረሻውን ስንብት ለማየት ይህን ይጫኑ

(አንድ አድርገን ነሐሴ 17 2004 ዓ.ም)፡- የብጹእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ስርዓተ ቀብር መንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተከናወነ ፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ ፤ የህዝብ ተወካች ምክር ቤት አፈጉባ አባ ዱላ ገመዳ ፤ ምክትል አፈጉባዬ ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ ፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ፤ የአኅት ቤተክርስትያን አባቶች ፤ በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ መንግስት አምባሳደሮች ፤ እና የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት በዛሬው እለት ስርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል ፡፡

ትላንት ማታ በሰረገላ ታጅቦ ከመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ወደ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል በርካታ በብጹዓን ጳጳሳት በክቡራን ሚኒስትሮችና የመንግስት ባለስልጣናት ፤ የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎች ፤ በሊቃውንተ ቤተክርስትያን በሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ፤ በአዲስ አበባ ፖሊስ ሰራዊት ባንድ ፤ በምዕመናንና በምዕመናት በክብር ታጅቦ መሄዱ ይታወቃል ፤ ረቡዕ ለሊት ከምሽቱ 2፡00 ጀምሮ እስከ ንጋቱ ድረስ ለሊቱን በሙሉ ጸሎተ ማህሌት ሲከናወን አድሯል ፤ ንጋት 12፡30 ላይ አስከሬኑ ባለፈበት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል በብጹአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና አኅት አብያተክርስትያን ተወካዮች ባሉበት ስርዓተ ቅዳሴው ተከናውኗል ፤ ጸሎቱ እንዳበቀ የቅዱስነታቸው አስከሬን በክብር ታጅቦ ወደ አውደ ምህረት ወጥቷል በተዘጋጀለት ቦታ ላይ ለሰዓታት አርፏ ፡፡

የወጣው መርሀ ግብር በተቀመጠለት ሰዓት በአግባቡ በማከናወን ዛሬ ነሐሴ 17 ፤ 2004 ዓ.ም የብጹዕ ወቅዱስ ደ/ር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የአለም የአብያተክርስትያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ፤ የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት ፤ የዓለም ሰላም አምባሳደር ስርዓተ ቀብር ከቀኑ 7፡30 ተፈጽሟል፡፡

“አንድ አድርገን”፡- የአባታችንን ነፍስ እግዚአብሔር ከአብርሀም ከይስሀቅ እና ከያቆብ ጎን ያሳርፍልን 

No comments:

Post a Comment