Tuesday, December 2, 2014

የአለቃ አያሌው መጽሐፍ ከ54 ዓመት ቆይታ በኋላ ዳግም ለህትመት በቃች


አንድ አድርገን ኅዳር 24 2007 ዓ.ም
ታላቁ አባትና የተዋሕዶ አይን የነበሩት አለቃ አያሌው ታምሩ  አባ አየለ ተክለ ሃይማኖት የተባለው ካቶሊካዊ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ስለ ክርስቶስ ባሕርያት አካላዊ ተዋሕዶ የምታምነው ትምህርት በሚል ስም በ1951 ዓ.ም ላሳተመው መጽሐፍ ሙሉ መልስ ሆኖ የተዘጋጀው ‹‹መች ተለመደና ከተኩላ ዝምድና›› የሚለው በአባታችን የተጻፈው መጽሐፍ ከ54 ዓመት በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ በአለቃ አያሌው ቤተሰቦቻቸው አማካኝነት የአባታችንን ዕረፍት 7ተኛ ዓመት መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ መጽሐፏ ለህትመት አብቅተዋታል፡፡

ክቡር አባታችን አለቃ አያሌው ታምሩ ‹‹መች ተለመደና ከተኩላ ዝምድና›› የተሰኝውን መጽሐፍ ያዘጋጁት ከ50 ዓመት በፊት ነበር፡፡ ለዝግጅቱ መንስኤ የሆነው ዶ/ር አባ አየለ ተክለሃይማኖት የተባሉ ካቶሊካዊ መነኩሴ የጻፉት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ስለ ክርስቶስ ባሕርያት አካላዊ ተዋሕዶ የምታምነው ትምህርት የተሰኝ መጽፍ ነበር፡፡ ራሳቸውን አባ አየለን ጨምሮ በተለያዩ ጽሑፎች ላይ እንደተጠቀሰው መነኩሴው ይህን መጽሐፍ የጻፉት የዶክትሬት ድግሪአቸውን ለማግኝት ነበር፡፡ የኦርቶዶክስ አማኞች የሚያምኑትን ሳያውቁ ፤ ሳይረዱ ከካቶሊክ እምነት የተለየ ምንም እንደሌላቸው  ለመስበክ  በሞከሩት መጽሐፋቸው ላይ በአንባቢያን ለትዝብት የሚያበቃ ሆን ተብለው በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ላይ የተነጣጠሩ ብዛት ያላቸው ክፉ ሀሳቦችን በማንጸባረቃቸው የተነሳ በየጊዜው የነበሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተክርስቲያን ሊቃውንት የማያዳግም መልስ ተሰጥተዋቸዋል፡፡ ከነዚህ መልስ ሰጪ ሊቃውንት መካከል አባታችን ክቡር አለቃ አያሌው ታምሩ ነበሩ፡፡ ይህን መጽሐፍ በጊዜው በቤተ ክርስቲያን ላይ የተነሱ የተለያዩ ሃሳቦችን መልስ ሰጥቷል፡፡ ከዘመን በፊት የተነሱ ሃሳቦች ከዘመን በኋላም ሊነሱ የሚችሉ መሆኑን የተገነዘቡት አለቃ አያሌው ‹‹ ይህ መጽሐፍ ከ15ተኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በወንጌል ስም ወደ ኢትዮጵያ የሚወረወረውን የጠላት ጦር ኃይል የሚሰበርበት እንዲሆን አምላከ ጴጥሮስን አለምናለሁ›› ብለዋል፡፡

ይህችን መጽሐፍ ለማሳተም ለተባበራችሁ ሁላ እግዚአብሔር ይስጣችሁ፡፡


የመጽፍ ስም ፡- ‹‹መች ተለመደና ከተኩላ ዝምድና››

አዘጋጅ ፡- አለቃ አያሌው ታምሩ

የመጀመሪያ ህትመት ፡- መስከረም 30 1953 ዓ.ም

ሁለተኛ ህትመት ፡ ነሐሴ 2006 ዓ.ም

ዋጋ ፡- 75 ብር

No comments:

Post a Comment