Saturday, October 31, 2015

ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የ24 ሰዓት የቴሌቪዥን አገልግሎት ልትጀምር ነው

  • ለሳተላይት ሥርጭቱ 12. ብር በላይ ዓመታዊ በጀት ጸድቋል
(አዲስ አድማስ ጥቅምት 20 2008 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በሀገር ውስጥና በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ፣ ምእመና ድምፅዋን የምታሰማበትና መረጃ የምትሰጥበት 24 ሰዓት የቴሌቪዥን አገልግሎት እንድትጀምር ቅዱስ ሲኖዶስ ወሰነ፡፡

ከጥቅምት 12 ጀምሮ የዓመቱን የመጀመሪያ የምልአተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ በማካሔድ ላይ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ፣ የቴሌቪዥን አገልግሎቱን ለማስጀመር 12 ሚሊዮን ብር በላይ ዓመታዊ በጀት ከትላንት በስቲያ ማጽደቁ ታውቋል፡፡

"የነፍስ ወይንስ ከስጋ ፈውስ?"


(ያሬድ ሹመቴ)
 

(አንድ አድርገን ጥቅምት 20 2008 ዓ.ም)፡- ሰሞኑን በመምህር ግርማ መታሰር ዙሪያ የሚነሱ ክርክሮችን ስመለከት 20 ዓመታት ወደ ኃላ ተጉዤ አንድን ክስተስ እንዳስታውስ ምክንያት ሆነኝ። መምህር ግርማ በተከሰሱበት ወንጀን ነፃ መሆን አለመሆን ጉዳይ ምንም አይነት አስተያየት የሌለኝ ሲሆን እግዚአብሔር ሲፈቅድ እውነታውን ማወቅ እንደሚቻል በማመን ለሱ ትቼዋለሁ።

መምህር ግርማ የታሰሩት 800ሺህ ብር በማታለል ተጠርጥረው ነው



(አዲስ አድማስ ጥቅምት 20 2008 ዓ.ም)፡- መምህር ግርማ ወንድሙ የታሰሩት እምነትን መነሻ በማድረግ፣ በተፅዕኖ መኖሪያ ቤት በማሸጥና ገንዘብ አታሎ በመውሰድ ወንጀል ተጠርጥረው መሆኑን ፖሊስ ለፍ/ቤት ያስረዳ ሲሆን ተጠርጣሪው ግን አስተባብለዋል፡፡

ባለፈው ረቡዕ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት በኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ዘንድ በአጥማቂነት የሚታወቁት መምህር ግርማ ወንድሙ፤ በተጠረጠሩበት ወንጀል ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ያስፈልገኛል በማለቱ /ቤቱ 7 ቀን ሰጥቷል፡፡

Thursday, October 29, 2015

‹‹መምህር›› ግርማ የተጠረጠሩበት ወንጀል ዝርዝር ይፋ ሆነ



አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18 2008 (ኤፍ..) ትናንት በቁጥጥር ስር የዋሉት መምህር ግርማ ወንድሙ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።መምህር ግርማ ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄም ወድቅ ተደርጓል።የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የፖሊስ መርማሪ ቡድን ዛሬ ግለሰቡን በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1 የወንጀል ችሎት አቅርቧቸዋል።ፖሊስ ግለሰቡ በተጠረጠሩበት የማታለል ወንጀል ቀሪ የምርመራ ስራ ስላሉብኝ ተጨማሪ 14 ቀን ይፈቀድልኝ ብሏል።

ተጠርጣሪው በራሳቸውና በጠበቃቸው በኩል ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ ጊዜ  በመቃወም የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ጠይቀዋል። የፖሊስ የምርመራ ቡድን በበኩሉ እሳቸው ቢለቀቁ ሌሎች ተፈላጊዎችን እና የተለያዩ ሰነዶችን ስለሚያሸሹብን ጥያቄያቸው ውድቅ ይሁን ብሏል።ፍርድ ቤቱ የሁለቱንም ወገን ክርክር መርምሮ ፖሊስ አብዛኛውን የምርመራ ስራ ያካሄደ በመሆኑ ለቀሪ የምርመራ ስራዎቹ ይረዳል በማለት ከጠየቀው 14 ቀን ጊዜ ውስጥ 7 ቀን ብቻ ፈቅዷል።ውጤቱን ለመጠባበቅም ለጥቅምት 25 2008 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

Sunday, October 25, 2015

ቅዱስ ሲኖዶስ በ“ተሐድሶ ኑፋቄ” እና በሙስና ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል




በቤተ ክርስቲያኒቷ ስም በብዙኃን መገናኛ ስለሚተላለፉ ትምህርቶች ይወስናል

 (
አዲስ አድማስ ጥቅምት 13 2008 ዓ.ም)፡-  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፣ የቤተ ክርስቲያኒቷን ቀጣይ ህልውና እየተፈታተኑና የምእመናኗን ፍልሰት እያባባሱ ናቸው በተባሉ፤ ተሐድሶ ኑፋቄእና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ በጥልቀት በመምከር ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ተገለጸ፡፡የቅዱስ ሲኖዶሱ የመጀመሪያ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ፣ ከትላንት በስቲያ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በመክፈቻ ጸሎት ሥነ ሥርዐት የተጀመረ ሲሆን በምልአተ ጉባኤ የተሠየመው አጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴ በቀረፃቸውና በምልአተ ጉባኤው በጸደቁ የመነጋገርያ ነጥቦች ለቀናት እንደሚመክር ታውቋል፡፡