Saturday, January 23, 2016

በ“ኦርጋን” ብንዘምር ምን አለበት?



ከጥንት ጀምሮየምን አለበት?” መዘዙ ብዙ ነው፥የግድ የለሾች መፈክር ነው።እግዚአብሔር መሐሪ ስለሆነ ኃጢአት ብሠራ ምን አለበት?” እንደ ማለት ነው።ንስሐ ከመግባት ይልቅ እግዚአብሔርን መሞገት የፈለገ ሰው፡-“ኰንኖ ኃጥአን ኵሎሙ ኢይደልወከ ምንተ ፥አፍቅሩ ጸላእተ ክሙ እንዘ ትብል አንተ ፤ፈራጅ ዳኛ እግዚአብሔር፡-በጠላቶችህ ኃጥአን ላይ ልትፈርድ አይገ ባህም፥አንተ ጠላቶቻችሁን ውደዱ ብለሃልና፤በማለት እንደተናገረውም ሊሆን ነው።ወይም ሲቆርብ ሲያቆርብ የኖረ በደለኛ ሰው፥ንስሐ ከመግባት ይልቅ፡-“ዘበልዐ ሥጋየ ወዘሰትየ ደምየ፥ ሕይወት ዘለዓለም የሃሉ ምስሌየ፤ብለህ ተናግረህ፥በወንጌል ተጽፎ ይገኛል ቃልህ፤ይኸንን ተላልፈህ ተኰነን ብትለኝ፥አብረን እንወርዳለን እኔ ምንቸገረኝ፤በማለት እንዳፌ ዘው መሆኑ ነው። -አዳምና ሔዋን በምክረ ከይሲ ተነድተው፥በምን አለበት? የዕፀ በለስን ፍሬ መብላታቸው አልጠቀማቸውም። ዘፍ፡፪፥፲፯።

ቃየል ሥርዓተ መሥዋዕትን ንቆ በምን አለበት? ያቀረበ ውን መሥዋዕት እግዚአ ብሔር አልተቀበለውም፤ወንድሙንም በምን አለበት? ገድሎታል።ዘፍ፡፬፥፫።ዔሳው በምን አለበት? ሥርዓተ ብኵርናን በማቃለሉ፥በረከተ ምርቃትን አጥቶአል።ዘፍ፡፳፭፥፴፬።ዳታን፣አቤሮንና ቆሬን በምን አለበት? ሥርዓተ ምስፍናን እና ሥርዓተ ክህነትን በመ ጋፋታቸው፡-መሬት ተከፍታ ዋጠቻቸው፥እሳትም ከሰማይ ወርዳ፡-አቃጥላ ገደለቻቸው እንጂ አልተጠቀሙም።ዘኁ፡፲፮፥፩-፶።አካን በምን አለበት?ከኢያሪኮ ምርኰ ወስዶ በመደበቁ፥እግዚ አብሔር ገልጦበት፥በድንጋይ ተቀጥቅጦ ሞቶአል።ኢያ፡፯፥፲፰።የአሮን ልጆች ናዳብና አሚናዳብ -በምን አለበት?ከሥርዓቱ ውጭ፥እግዚአብሔር ባላዘዛቸው እሳት የዕጣን መሥዋዕት በማቅረ ባቸው፥እሳት ከሰማይ ወርዶ፥ተቃ ጥለው በእግዚአብሔር ፊት ሞተዋል።ዘሌ፡፲፥፩።

የዔሊ ልጆች አፍኒን እና ፊንሐስ፡-በምን አለበት?ወደ እግዚአብ ሔር ቤት ከሚመጡ ሴቶች ጋር በማመንዘራ ቸው፡-እግዚአብሔር ፍልስጥኤማውያን አስነሣባቸው፥እነርሱም በጦርነቱ ላይ ሞቱ፥ታቦተ ጽዮንም ኃይሏን በእሕዛብ ምድር እስክትገልጥ ድረስ ተማረከች።ሊቀ ካህናቱ ዔሊም ከሥር ዓተ ቤተ መቅደሱ ይልቅ ለልጆቹ በማድላቱ፡-ከወንበር ወድቆ፥አንገቱ ተቆልምሞ ሞቶአል። ፩ኛ፡ሳሙ፡፬፥ -፳፪።ንጉሡ ዖዝያን፡-ሥር ዓተ ክህነትን እና ሥርዓተ ቤተ መቅደስን በምን አለ በት? አቃልሎ፥ጥና ይዞ ለማ ጠን ወደ ቤተ መቅደስ በመግባቱ እግዚአብ ሔር በለምጽ ቀስፎ ታል።እርሱ ደግሞ እግዚአብሔር ቀስፎት ነበ ርና ይወጣ ዘንድ ቸኰለ፤ይላል።፪ኛ፡ዜና፡፳፮፥ ፲፯።ዖዛ፡-በምን አለበት? የእግዚአብሔርን ታቦት በመያዙ፥የእግ ዚአብሔር ቍጣ እንደ እሳት ከነደደበት በኋላ በታቦቱ ፊት ሞቶአል ።፪ኛ፡ሳሙ፡፮፥፩-፲፩።

የቤት ሳሚስ ሰዎች ካህናት ሳይ ሆኑ በምን አለበት? የእግዚአብሔርን ታቦት ገልጠው በማየታቸው፥ እግዚአብሔር፡-ከሕዝቡ መካ ከል ከአምስት ሺህ ሰዎች ሰበዓውን በሞት ቀጥቶአቸዋል።ሕዝቡም የእግዚአብሔርን ቅጣት አይተው አለቀሱ፤በዚህ በቅዱስ አምላክ በእግዚአብሔር ፊት ማን መቆም ይችላል?” አሉ።በዚህምበታቦት ፊት መቆም፡-በእግዚአብሔር ፊት መቆም፥ታቦትን መድፈር ደግሞ፡-እግዚአብሔርን መድፈር መሆኑን መስክረዋል።፩ኛ፡ሳሙ፡፮፥፲፱።
 
ንጉሡ ሳኦል፡-ነቢዩ ሳሙኤል፡- “ወደ አንተ መጥቼ መሥዋዕት እስክሠዋ ድረስ ሰባት ቀን ትቆያለህ፤ያለውን ትእ ዛዝ አቃልሎ ፥በምን አለበት ሠውቶ በመቆየቱ፡-“እግዚአብሔር ያዘዘህን አልጠበቅህምና መንግሥትህ አይጸናም ብሎታል። ፩ኛ፡ሳሙ፡ ፲፥፭፤፲፫፥፰።አማሌቃውያንን እንዲወጋ በታዘዘ ጊዜ፥ምርኰ እንዳይሰበስብ ተነግሮት ነበር። እርሱ ግን በምን አለበት? ምርኰ ሰበሰበ፥እግዚአብሔርም ተቆጣበት። ነቢዩ ሳሙኤል ቢጠይቀው፡-“የሰባ የሰባውን ከብት ለእግአብሔር እሠዋለሁ ብዬ ነው፤አለው።ነቢዩም፡-“እግዚአብሔር ናቀህ፤አለው፥ ርኵስ መንፈስም ተቆራኝቶት ተሠቃየ። ፩ኛ፡ሳሙ፡፲፭፥ -፴፭።

የናቡከደነጾር ልጅ ብልጣሶር፡-በምን አለበት?በቤተ መቅደሱ ንዋያተ ቅዱሳት በመመ ገቡ እግዚአብሔር ተቆጣበት፥ዕለቱኑ በጠላቶቹ ተገደለ። ዳን፡፭፥፩-፴፩። ሐናንያና ሰጲራ -ሥር ዓተ ቤተ ክርስቲያን በሚያዘው መሠረት ሙሉ ሀብታቸውን ማስረከብ ሲገባቸው በምን አለበት? ግማሹን ደብቀው አስቀሩ። ቅዱስ ጴጥሮስ በጠየቃቸውም ጊዜ በምን አለበት? በመዋሸታቸው በየተራ ተቀስፈው ሞቱ።የሐዋ፡፭፥፩-፲፩።

የአስቄዋ ልጆች ደግሞ ጸጋውም ሥልጣኑም ሳይኖራቸው፥ በምን አለበት? አጋንንት ለማስወጣት ተሰለፉ።ክፉው መንፈስ ግን መልሶ፡-ኢየሱስን አውቀዋለሁ፥ ጳውሎስንም አውቀዋለሁ፥ እናንተስ እነማን ናችሁ?”አላቸው ፥ እስኪቆስሉ ጨርቃቸውንም ጥለው እስኪሸሹ ድረስ በረታባቸው፥አሸነፋቸውም፤ይላል። የሐዋ፡፲፱፥፲፬።  

እንግዲህ ከላይ እንዳየነው የምን አለበት? የምን ችግር አለው? መዘዙ፡-ብዙ፥የብዙ ብዙ ነው። በኦርጋኑ ብቻ የሚያቆም አይደለም፥ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፡-ሙሉ በሙሉ ወደ ፕሮቴስታንት ነት እስክትለወጥ ድረስ የሚቀጥል ነው። ባለፈው፡-የቀድሞው አባ ሀብተ ማርያም የአሁኑ አባ መልከ ጼዴቅ፡-በንጉሡ ዘመን ኦርጋኑን ወደ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የማስገባታቸውን ገድል ተናግረዋል። ያልተናገሩት፡- ኦርጋኑ ገብቶ ስንት ሰው ከቤተ ክርስቲያን እንዳስወጣ ፥ ስንት ሰው ወደ ፕሮቴስታንትነት እንደተለወጠ ነው። የሃይማኖት አበው ማኅበር፥ የአዲስ አበባ የልደታ ሰንበት /ቤት ፥ የባህርዳር ጊዮርጊስ ሰንበት /ቤት ፥ የሀረር ሥላሴ ሰንበት /ቤት አባላት የነበሩት አሁን ያሉት የት ነው? እርሳቸው ባይናገሩትም፡- የፕሮቴስታንት ፓስተሮች፡-በየጋዜጦቻቸውና በየመጽሔቶቻቸው ከእኛ ጋር ተቀላቅለዋል እያሉን ነው፥ ማኅበረ ቅዱሳን እንቅፋት ባይሆንብን ኖሮ እስከ ዛሬ ኦርቶዶክስን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረናት ነበር፤እያሉን ነው። እነአባዮናስ ዛሬ የፕሮቴስታንት መጋቢ ናቸው። እነ መልአኩም የፕሮቴስታንት ፓስተር ከሆኑ በኋላ ለምን ተመልሰው የኦርቶዶክስ ቄስ እንደሆኑ፥ የሚያውቁት፡-ፕሮቴስታንቱ መልአኩና ክህነት የሰጡት አባ መልከ ጼዴቅ ብቻ ናቸው። እኛም እናውቃለን፥ ትናንት ያቆሰሏትን ቤተ ክርስቲያን ለመግደል ነው።ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን፡-ሞትን ድል አድርጐ የተነሣ አምላክ የኢየሱስ ክርስቶስ አካል በመሆኗ አትሞትም።ይህ አውነት ነው፥

6 comments:

  1. read this https://www.facebook.com/photo.php?fbid=441348276064052&set=p.441348276064052&type=3

    ReplyDelete
  2. ewnt sfhal wgana enab malkasadek orthodox twhdowen eybrezw ythdesow msly washa adrgawatal Ethiopia menmenw snkabachew stawekem mtalyachew American honewas men albet awdemherat ly tabot kemew ywest astdadern guday ysanbet tmarewec nen ymelew endyakerbwen emdrbsw tabaten men albet eyalew ymelew bmkedes west ymysrebesew astmarewch yayanebt zamen ktwgazwe astmarewech gar gbay ymserwe ezhew ynmnalbet yharea tek geday asfsamewechem ezhew alew gabez menmen nek enantenem deferet eystmarew yleweten men alabet ganzab bch ysgag ing mkedeswem mfencyhachew honwel btcresthanachenn entabk wrwenal zare mhber kidisan any yalwet ewntza nlbtkrestynen tofet dakm knona slmykbrewn ydengle Mary me lgwech slhonew bch new nekw endantafa wgnwech !!ydengle Maryam yasrat legwech agaltewen ewntew tawekew holem ygadale gadame bech aydelem katamam sl hymanot mgadel al nk!nk ega bnsh entadsalen tfatachenn aweka nsa kgba b tchresteanchen ge abtchache btre mesrt tlwele ylfw sendew embet nech attdesem tadsalec eng!! egezabher amlk ydengl Maryam leg btcrectinen ytabkele aman!!aman! aman!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

    ReplyDelete
  3. abatachin kalehiwot yasemalin gin ene yemilewu lela neger alegn minalebet tikikilegna yetehadiso mefekir endehone yigebagnal gin ezih north america yalu behager bet sinodos sir yemitedaderu abiyate kiristiyanat meche yerasachewun chigirna tifat tewetut lemisale bemebetachin ken wer begeba be 21 kidase mariyam mekedes sigebachewu kidase hawariyat yikedisalu beametu michael ken yaekob ze sirug mekedes sigebachewu kidase hawariyat yikedisalu yih minalebet ayidelem lelawu yikirina 2 kes eyale enkua be 1 kahin yikedisalu be ewunet yih siriat newu abatochachin yasirekebun tiwufit yih newun? tamire mariyam yimiyanebut beabizahagnwun gize sile bisirat ena 5tun yemebetachin hazenat bicha newu ewun tamiremariyamin yafirubetal weyis? be ewunet bizu chigir ale mezerzer yichalal ene yemilewu gin hulum be organ mezemerim be 1 kahin mekedesim be mebetachin kenina be michael ken kidase hawariyat mekedesim yaferese diyakon betemekides masigebatim lene minalebet weyim yetehadiso sera newu minalibat yihin neger tenegagirachihu 1 belut lenegewu terekabi tiwulid yetebelashe ena yetebereze siriat eyastemarut eyaweresun newu ere babatochachin amilak yihunibachihu tesebisibachihu siriatun asitekakilut

    ReplyDelete
  4. Comment by Feleke: አርጋኖን በቤተ ክርስተያን አገልግሎት ላይ መዋል ያስፈልገዋልን? በመሠረቱ ይህን ጥያቄ በቀጥታ ከመመለሳችን በፊት በቤተ ክርስቲያናችን መዝሙራትን በአማርኛ መዘመር የተጀመረው መቼ ነው? ለዚህም ጥቂት ማብራሪያ መስጠቱ ያስፈልጋል። ከጥንት ጀምሮ በቤተ ክርስቲያናችን ግልጋሎት፣ ምስጋና የሚደርሰውና የሚቀርበው በግእዝ ቋንቋ ነበር። በኢትዮጵያ፣ ወጣቶች መዝሙራትን በአማርኛ ቋንቋ እንዲዘምሩ ለመጀመሪያ ጊዜ መጽሐፍ የተዘጋጀው እ.ኢ.አ በ፲፱፻፵ (1940)ዎቹ ላይ መንፈሳዊ ማኅበራት (ሰንበት ት/ቤት) ገና መቋቋም እንደጀመሩ ነው (1)። በወቅቱ የነበሩት የቤተ ክርስቲያን አባቶች በሰጡት ትእዛዝ መሠረት ወጣቱ ወደ ሌሎች የሃይማኖት ድርጅቶች እንዳይሄድ በብዛት የአማርኛ መዝሙራትን በማዘጋጀት መንፈሳዊ ማኅበራትም በየአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑ እንዲቋቋሙ ከፍ ያለ ጥረት ተደርጓል። በዚያን ወቅት፣ “እንደ ቸርነትህ”(1A) የሚለው እስከዛሬ ድረስ እጅግ ተወዳጅ የኾነው መዝሙርና ሌሎችም መዝሙሮች በአቶ ኢሳይያስ ዓለሜ የኖታ ምልክት ተደርጎላቸው (ተደርሰው) የቤተ ክህነቱንም ይኹኝታ አግኝተው በኦርጋን (በአርጋኖን) አጃቢነት መዘመር የተጀመረው፣ ከዚያን ወቅት ማለት እ.ኢ.አ ከ፲፱፻፵፮ (1946) ዓ ም አንስቶ ነው። እነዚህም መዝሙራት፤ ከዚያ ጊዜ አንስቶ በመጽሐፍ መልክ ታትመው እገበያ ላይ በማዋል ማኅበራቱ ሲጠቀሙባቸው ይኼው እስከ ዘመናችን ደርሰዋል ለሃምሳ ሰባት ዓመታት። በዚያን ጊዜ መዝሙራት ሲደረሱ እንዲህ እንደ ዛሬው ማንም ዝም ብሎ ከመሬት ተነሥቶ ዘማሪ/ዘማሪት እገሌ ብሎ በገዛ ራሱ ብቻ መዝሙር ደረስኩ በማለት በካሴት ማውጣት አይችልም ነበር፤ በቅድሚያ ለቤተ ክህነቱ ማለትም ለበላይ አባቶች አቅርቦ ከተመረመረና ክተፈቀደ በኋላ እንጂ። ለምሳሌ አቶ ኢሳይያስ ዓለሜ የመዝሙር መጽሐፉን አዘጋጅተው በኖታ ሲያቀርቡ በወቅቱ የሊቀ ጳጳሱ የብፁዕ አቡነ ባስልዮስ እንደራሴና የነበሩት የሐረር ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ ሌሎች ኹለት/ሦስት መምህራነ ቤተ ክርስቲያንን ጨምረው አይተውና መርምረው ከፈቀዱ በኋላ ነበር የታተመው ። ከዚያን ጊዜ በኋላ የተደረሱ መዝሙራትም በተመሳሳይ ኹኔታ ተመርምረው እየተፈቀዱ ነበር በየቤተ ክርስቲያኑ ሲዘመሩ የቆዩት። የተደረሱትም መዝሙራት ይበልጥ በሕዝብ ዘንድ እንዲታወቁና እንዲለመዱ በማሰብ ቤተ ክርስቲያናችን በ፲፱፻፷ (1960)ዎቹ መጀመሪያ ላይ በወቅቱ ታዋቂ በነበረው ክብር ዘበኛ የሙዚቃ ባንድ ጦር በርካታ መዝሙራት በዘመናዊ መሣሪያ ታጅበው እንዲዘመሩ አድርጋ ለምዕመናን ተሰራጭተዋል ። እንዲሁም የሙዚቃ ችሎታ ያላቸው ባለሙያዎች በየአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናቸው መዝሙራትን በዘመናዊ መሣሪያ አጅበው በመጫወት መዝሙራቱ የበለጠ ተወዳጅነትን አትርፈዋል። ይኽንንም ከፍ ያለ አስተዋጽኦ በማየት ቤተ ክርስቲያናችን ለእነዚያ የሙዚቃ መሣሪያ ባለሙያዎች የምስክር ወረቀት በመስጠት ታበረታታ ነበር ። ከዚህም የተነሳ አርጋኖን (ኦርጋን) በብዙ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ አጃቢ መሣሪያ ሆኖ ቈይቷል። ከዚያ ጊዜ አንሥቶም፤ እንደ ሊቀ መዘምራን ኪነ ጥበብ እና እንደ መሪጌታ ፀሐይ ብርሃኑ ያሉት ጣእመ ዝማሬያቸው እስከ ዛሬ ድረስ ተሰምቶ የማይጠገበው የቤተ ክርስቲያኒቱ ታዋቂ ልጆችና ሌሎችም በአርጋኖን የታጅቡ መዝሙራትን አዘጋጅተው በካሴት ስላቀረቡ የአማርኛ መዝሙራት ይበልጥ ተወዳጅ እየሆኑ መጡ። እነዚያ በኦርጋን ታጅበው የተዘመሩ መዘሙራት ዛሬም ድረስ ምዕመናኑን ለቃለ ስብከቱ አገልግሎት ይበልጥ ለማዘጋጀት በሀገራችን በየአብያተ ክርስቲያናቱ ይዘመራሉ ። ይህ በእንዲህ እያለ ከ፲፱፻፹ 1980ዎቹ አጋማሽ አንስቶ “በሀገር ባህል መሣሪያ እንጂ፣ በባእድ መሣሪያ በአርጋኖን መዘመር የለበትም” የሚሉ ወገኖች ተነስተው በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ክፍፍል እንዲነሣ ስላደረጉ፤ ይህን ችግር ለመፍታት ሲል ቅዱስ ሲኖዶስ በግንቦት ወር ፲፱፻፷፮(1986) ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መሣሪያዎች በአጃቢነት ሥራ ላይ እንዲውሉ ወስኗል፦ ዋሽንት፣ ከበሮ፣ ጸናጽል፣መሰንቆ፣በገና፣እምቢልታ፣አርጋኖን/ኦርጋን -(ክራር ያልተፈቀደ መሣሪያ መሆኑን እዚህ ላይ ማስተዋል ያሻል)። ኦርጋን ወይም አርጋኖን ማለት ምን ማለት ነው? ስለ ትርጓሜው በተለያዩ መዝገበ ቃላት ላይ የተገለጸውን ይመልከቱ ። እነዚህ ኦርጋን የሚለውን ቃል ጆሮአቸው መስማት የማይፈልጉ ተመጻዳቂዎች አባባላቸው ትክክል አለመኾኑን ልቡናቸው እያወቀ፣ ላለመሸነፍ ብቻ አርጋኖን ማለት አባ ጊዮርጊስ ስለ እመቤታችን ፍቅር የደረሰላት የመጽሐፈ ስም እንጂ መሣሪያ አይደለም እስከ ማለት ደርሰዋል – ታላቅ ትዝብት። በመሠረቱ ቅዱስ ሲኖዶስም መሣሪያ ባይኾን ኖሮ፤ ከተፈቀዱ መሣሪያዎች እንደ አንዱ አድርጎ ባልቈጠረውም ነበር። ስለዚህ የእነዚህ ሰዎች ክርክር እንዲሁ የአልሸነፍም ባይነት እንጂ፣ በቂ ማስረጃ ሊያቀርቡለት የማይችሉ በመኾናቸው ተቀባይነትም፣ አሳማኝነትም አይኖረውም – ፈጽሞ። ኦርጋን በቅዱስ ሲኖዶስ የተፈቀደ መሣሪያ ሆኖ ሳለ፣ በኦርጋን መጠቀም ክልክል ነው የሚለው ሓሳብ ከየት መጣ?

    ReplyDelete
  5. The old outdated Orthodox politics 'የምን አለበት? የምን ችግር አለው? መዘዙ፡-ብዙ፥የብዙ ብዙ ነው። በኦርጋኑ ብቻ የሚያቆም አይደለም is back again "What drives members out is not musical instrument, it is bad administration specially with restless and busy diaspora. The Ethiopian Orthodox church has fought so many things in my time that will enhance, modernize, strength the church and its members. We do not have to fear what comes, instead we should see if it helps. Modern church uses Organ and see no problems. Using Organ does not have any thing to do with Protestantism. Let us not spend our time with small things we have more to do, hunger poverty relentless oppression of our people by TPLF. Let us spend our time fighting poverty and oppression

    ReplyDelete
  6. https://www.youtube.com/watch?v=RFyJY5ytM1Q

    ReplyDelete