Sunday, July 17, 2016

የራሳቸው ሰዎችን ፊርማ ለአስመራጭ ኮሚቴው ያቀረቡ ፡ አባ ሚካኤል ገብረማርያም

(አንድ አድርገን ሐምሌ 10 2008 ዓ.ም) እስከ አሁን ድረስ በተለያዩ መንገዶች የተጠቆሙ እና አስመራጭ ኮሚቴው እንደተቀበላቸው ከተገለጹት ቆሞሳትና መነኮሳት ስም ዝርዝር ውስጥ  አባ ሚካኤል ገብረማርያም ይገኙበታል፡፡
የከምባታ እና ሀላባ አካባቢ ሕዝብ ደግፎኛል በሚል አሰባሰብኩ ያሉትን የራሳቸው ሰዎችን ፊርማ ለአስመራጭ ኮሚቴው ያቀረቡት አባ ሚካኤል ገብረማርያም የከምባታ አላባ /ስብከት ስራ አስኪያጅ በዱራሜ ከተማ የሚገኘውን የጥምቀት በዓል ማክበሪያ ቦታን ከመናፍቃን ጋር በመሆን ያላቸውን የፖለቲካ ተቀባይነት ለማሳደግ ሲሉ አሳልፈው በመስጠጥ የሚታወቁ ፤ የቤተክርስቲያንን እርስት አሳልፈን አንሰጥም ያሉ የቤተ ክርስቲያናችን ተቆርቋሪዎችን አባቶቻችንን  ሽብርተኞች እያሉ የሚያሸማቅቁ ፤ በአውደ ምህረት እንዳያስተምሩ የታገዱትን የተሀድሶ ሰባኪያንን እርሳቸው በሚያስተዳድሩበት ሀገረ ስብከት እንደፈለጉ እንዲፈነጩበት በመፍቀድ(ለምሳሌ እነ በጋሻው በዱራሜ ተክለሃይማኖት ያደረጉት) አይሆንም የሚሉትን የቤተክርስቲያን ልጆች ደግሞ የተለያዩ ፖለቲካዊ አቅማቸውን በመጠቀም በማሸማቀቅ እና ባስ ሲልም በዛቻ እና በማስፈራሪያ እየታገዙ እጅግ ጥቂት አማንያን ያሉበትን አካባቢ እያወኩ የሚገኙ ሰው ናቸው፡፡


የጳጳሳት አስመራጭ ኮሚቴ ስለ አባ ሚካኤል ገብረማርያም የጀርባ ታሪክ እንዲያጠና ፤ የተለያዩ ማረጃዎችን ከሚገኙበት ሀ/ስብከት እንዲሰበስብ በአካባቢው የሚገኙ ምዕመናን ለአንድ አድርገን በላኩት ማስረጃ ጠይቀዋል፡፡

ነቀፌታ የሌለባቸው ለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዘብ ሆነው መቆብ የሚችሉ ፤ ቤተ ክርስቲያን ያለችበትን የወቅቱ ፈተና በመገንዘብ የመፍትሄ አቅጣጫ የሚያመላክቱ ፤ የተሰጣቸውን ከባድ ሃላፊነት በአግባቡ ሊወጡ የሚችሉ አባችን እናገኝ ዘንድ ሁሉም ምዕመን ስለተጠቆሙት አባቶች ያለውን መረጃ አስመራጭ ኮሚቴው ጋር እንዲደርስ የበኩሉን ሚና መጫወት ይኖርበታል፡፡


ለነገ የተሻለ አውድ ዛሬ አብረን እንስራ

No comments:

Post a Comment