Friday, July 8, 2016

አባ ናትናኤል ከጵጵስና ውድድሩ ራሳቸውን በይፋ ካላገለሉ በቀጣይ ሌሎች ማስረጃዎችን ይፋ ለማድረግ እንገደዳለን!


ለምዕመናንና ለሚመለከታችሁ አካላት በሙሉ
አባ ናትናኤል የአየር ጤና ኪዳነምህረት አስተዳዳሪ ሆነው የተሸሙት ታኅሳስ 2005 ነው፡፡ አዋሳ ስላሴ / አስተዳዳሪ ከነበሩበት ከተሃድሶውን ጋር አብረው በፈጠሩት ሁከት፣ ዝርፊያ፣ የሰው ነፍስ ማጥፋት ሙከራ፣ የስነምግባር ችግር ተወንጅለው ከተባረሩ በኋላ ነበር በቀጥታ እኛ ጋር የተመደቡት፡፡ ላለፉት 4 ዓመታት ያው ባህሪያቸው እዚህም ሲያውክ ቆይቶ አሁን ደግሞ ለጵጵስና መታጨታቸው ስለተሰማ የአየር ጤና ምዕመን በየጊዜው ለሀገረስብከቱ ሲያቀርባቸው የነበሩ አቤቱታዎችን፣ ደካማ የአስተዳደር አቅማቸውንና ግልጽ የሙስና ተግባራቸውን የሚያሳዩ ማስረጃዎች ብቻ ቆንጥረን ይፋ ለማድረግ ተገደናል፡፡   ከጵጵስና ውድድሩ ራሳቸውን በይፋ ካላገለሉ ግን በቀጣይ ሌሎች ማስረጃዎችን ይፋ ለማድረግ እንገደዳለን!

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!


ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ
                                                           ጉዳዩ፡- አቤቱታ ስለማቅረብ

እኛ የአየር ጤና / ኪዳነምህረት ካቴድራል በሰበካ ጉባዔ የምዕመናን ተወካዮች፣ የሰ//ቤት አባላት፣ የትምህርት ኮሚቴ አባላት፣ የልማት ኮሚቴ አባላት፣ የወጣት ማህበራት፣ የአካባቢ ሽማግሌዎችና የሰላም ኮሚቴ አባላት በደብሩ ጥቂት የአስተዳደር ሰራተኞች እየተፈጸሙ ያሉ ስህተቶች እየተበራከቱ መሄዳቸው በእጅጉ አሳስቦናል፡፡ ከደብሩ አስተዳደር፣ ከሰበካ ጉባዔ አባላት፣ ከክ/ከተማው ቤተክህነት፣ ሁኔታዎች ሲያስገድደንም ከመንግስት የአስተዳደርና የጸጥታ ክፍል ጋር ሁሉ በየደረጃውና በየወቅቱ ስንነጋገርበት ቆይተናል፡፡ ይሁን እንጂ የደብሩ አስተዳደር አሁን ባለበት ሁኔታ ተስፋ አስቆራጭ ሆኖብናል፡፡  በዚህ ምክንያትም የበላይ አባቶቻችን ለጉዳዩ መፍትሄ እንዲሰጡን በድጋሚ ማስቸገር እንዳለብን አምነን ለአቤቱታ መጥተናል፡፡ ባለፉት 3 ዓመታት የቻልናቸውና  ለምሬታችን ምክንያት የሆኑ ግድፈቶችን ከዚህ በታች በጥቂቱና በጥቅል ያስቀመጥን ሲሆን አሁን ተስፋ ለመቁረጥ ያደረሰንን ምክንያትና አቤቱታም አያይዘን አቅርበናል፡፡

. ጥር 2007 . በአባ ናትናኤል መላኩ የሚመራው የካቴድራሉ አስተዳደር ከዚህ በታች በተዘረዘሩ ጥፋቶቹ ምክንያት ቅሬታችንን አቅርበን ነበር፡፡
1.       ኮሚቴዎችን በቃለ አዋዲው መሰረት አለማደራጀትና አለማጠናከር እንዲያውም በተቃራኒው የማፍረስ ሚና በመጫወት ላይ መሆኑ፣ ለምሳሌ
ከሠበካ ጉባዔ ጋር፤ ከምዕመናን የሰበካ ጉባዔ አባላት ውስጥ /ሊቀመንበሩን በደብዳቤ እንዳይሰራ አድርገዋል፡፡ ሁለተኛው የምእመናን ተወካይና የሰንበት /ቤቱ ተወካይ  ተማረው እንዲያቆሙ አድርገዋቸዋል፡፡ ከምዕመናን በኩል አሁን ያለው ተወካይ አንድ ግለሰብ ሲሆን እሱኑልማት ኮሚቴ› ‹ትምህርት ኮሚቴላሉትም ሰብሳቢ አድርገውታል፡፡ ከካህናት ተወካዮች ውስጥም ስህተት የሚያርም አንድ ካህን ከደብሩ እንዲቀየር አስደርገዋል፡፡ ባለፉት ሁለት ዓመታት በሰበካ ጉባዔ ስም የሰሩት በዚህ ሁኔታ ሲሆን አሁን ደግሞ የሱም ጊዜ አልቋል፡፡
 ከሰ//ቤት ጋር //ቤቱን ለመበተን ተደጋጋሚ ጥረት አድርገዋል፣ አመራሮቹን ለማገድ ደብዳቤ ጽፈዋል፣ 8 ወራት የሰ//ቤቱን ስራ ማስኬጃ አግደዋል፣ የመማሪያ ክፍሎችን ከልክለው 4 ወራት የሰ//ቤቱን መርኃግብር አስተጓጉለዋል፣ በሰ/ጉባዔ ውስጥ የሰ//ቤቱ ተወካይ  እንዳይተካ አድርገዋል፣ ተደጋጋሚ ልመና ቢቀርብላቸውም አንድም ቀን በሰ//ቤቱ መርኃ ግብር ተገኝተው አስተምረው አያውቁም፡፡ የሰ//ቤት ወጣቶች የአገልግሎት ሰዓት እየታወቀ በተደጋጋሚ 100 በኋላ እንዳይመሽ የእገዳ ደብዳቤ ለፖሊስ ግልባጭ አድርገው መጻፍን ዋና ስራቸው አድርገዋል፣
 ከትምህርት ኮሚቴ ጋር፣ ነባሩን የትምህርት ኮሚቴ ያለምክንያትና እውቅና በትነዋል፣ በትምህርት አስተዳደር ውስጥ ጣልቃ በመግባት የትምህርት ስርዓቱን አውከዋል፣ የት/ቤቱን ገቢ ከሰ/ጉባዔ ገቢ ጋር ቀላቅለው የት/ቤቱን ዕድገት አኮላሽተዋል፣ ራሳቸው እንደአዲስ ያቋቋሙትን የትምህርት ኮሚቴምህግና ደንብ እንዲከበር የሚጠይቋቸውን አባላት በማገድ በትነውታል፣
ከልማት ኮሚቴ ጋር፤ የልማት ኮሚቴን ከቃለ-አዋዲው አሰራር ውጪ፣ ህዝብ ሳያውቀው  አደራጅተዋል፣ በልማት ኮሚቴው ላይ ሌላ ልማት ኮሚቴ አሁንም ከቃልአዋዲው ዕውቅና ውጪ አዋቅረዋል፣ ያለልማት ኮሚቴው ዕውቅና የስራ ውሎችና ጨረታዎች ተካሂደዋል፣ ህንጻ አሰሪ ኮሚቴውን ሊተካ በሚችል መልኩ የልማትና ህንጻ ኮሚቴ ስላልተቋቋመ ርክክብ እንዳይካሄድ እንቅፋት ሆኗል፣ ያው ያለአግባብ ያቋቋሙት ልማት ኮሚቴ አባላት በስማቸው የሚፈጸሙ ጥፋቶችን ሲቃወሙም በትነዋቸዋል፣

2.       ደብሯ ካላት የልማት ፍላጎት ጋር ሲተያይ አስተዳደሩ ደካማ አፈጻጸም ላይ ነው፣
በሰ/ጉባዔው ስትራቴጂክ ዕቅድ የደብሯን ልማት መምራት አልቻሉም፤ ታቦቱ ከገባ በኋላ ይሰራል የተባሉ ስራዎች አንዳቸውም ሳይሰሩ ከአንድ ዓመት በላይ አልፏል፡፡ ቅሬታ ካቀረብን በኋላ ባለፈው አንድ ዓመት የተጀመረው የበረንዳ ዕብነበረድ እና የዋናው መግቢያ ኮብልስቶን ስራም የገዘፈ የጥራት ችግር የታየበት ነው፡፡

3.       ስብከተወንጌል ከማስፋፋት ይልቅ እየጨለመ ነው፣
ስብከተ ወንጌሉ ያለኮሚቴና ዕቅድ እንዲሁ በዘፈቀደ  የሚካሄድ ሆኗል፤ ካህናትን ለስብከተወንጌል በዕቅድ የማሰማራት በስትራቴጂ ዕቅዱ የተቀመጠው አሰራር ባለቤት አጥቷል፤ አውደምህረቱ በጠዋትና በማታ የስም ማጥፊያ፣ የአድማ መፍጠሪያና የግል ስብዕና መገንቢያ መድረክ ሆኗል፤ በዕለተ ሰንበትና በበዓለት ምሽት የነበረው ሰፊ የስብከተወንጌል አገልግሎት ሞቷል፤ በስብከተ ወንጌሉ የሚጋበዙ መምህራን በመተዋወቅ የሚመጡ፣ የግለሰብ ስም የሚያሞግሱ እንጂ ወንጌል ለማስተማር አቅም የሚጎላቸው ሆነዋል፤ አገልግሎቱን ለመደገፍ በሰ//ቤትና በማህበራት የሚደረጉ እገዛዎች እንኳ ለውጥ እንዳያመጡ ሆን ተብሎ በአሰራር እንዲታነቅ ተደርጓል፡፡ ያለምክንያት የታገዱም አሉበት፡፡ በውጤቱም በዕለተሰንበትና በአበይት በዓላት እንኳ ምእመናን የማይገኙበት፣ የሚገኙትም አሜን ከተባለ በኋላ ግቢውን ለቀው የሚወጡበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ በአጠቃላይ የተላኩበት ስብከተወንጌልን የማስፋፋት ተልዕኮ ወደጎን ተብሏል፡፡

4.       ደንብና ስርዓት ያልተከተለ የፋይናንስና የሰው ኃይል አስተዳደር ስርዓት አንዲሰፍን ሆኗል፣
o   ጨረታዎች ያለሰበካ ጉባዔው ዕውቅናና ከህግና ደንብ ውጪ እየተካሄዱ ነው፣ ለአብነትም
§  የክሊኒክ ቦታው ለፓርኪንግ በሚል ጨረታ ወጥቶ ለቦለኬት ማምረቻ ተሰጥቷል፡፡ ይህ ሂደት ከመንግስት ፖሊሲ ጋር በመጋጨቱ እንዲቆም ሲደረግ ውሉ እንደሚፈርስ እየታወቀ ያለሰበካ ጉባዔው ዕውቅናና ከህግ ውጪ ከሌላ ሰው ጋር ውል ታድሷል፡፡ ይህ ህገወጥ ተግባር እንዲታረም ሲጠየቅም በሌላ ጨረታ ያው ንብረት በሌላ ሰው እንደተዛወረ ሆኖ ተላልፏል፡፡ 
§  የክሊኒክ ግንባታው በመቶሺህ ብሮች የሚገመት ስራ እንደመሆኑ በግልጽ ጨረታ ተወዳዳሪዎች መጋበዝ ሲገባቸውአጣዳፊ ነው በሚልምክንያት በውስን ጨረታ ግለሰቦች እንዲጋበዙ ተደርገዋል፡፡ ይህ ሳያንስም ውል የተፈጸመው ያለሰ/ጉባዔው ዕውቅና ነው፡፡ ይኽው ስራም ከቆመ ከዓመት በላይ ሆኗል፡፡ ለስራው ማስኬጃ ተብሎ ግን ቦታው ከላይ ባነሳነው ህገወጥ አካሄድ ለቦለኬት ማምረቻ ተከራይቷል፣
§  ለፓርኪንግ ተብሎ በወጣ ሌላ ጨረታ ቦታው ለጋራዥ ተከራይቷል፣ አሁን በተከራየው ቦታ ውስጥ ያለሰበካ ጉባዔው ዕውቅና ከአንድ በላይ ገራዥ አለ፣ ግዙፍ የመኪና ተረፈ-ምርቶች ማጠራቀሚያም ሆኗል፣
§  ያለሰ/ጉባዔው ውሳኔ ይዞታውን ሊያራቁት የሚችል የባህርዛፍ ጨረታ ወጥቶ በህዝብ ግፊት እንዲቆም ተደርጓል፣
§  የስዕል ጨረታ ከህግና አሰራር ውጪ፣ የቤ/ክኗንና የምዕመናንን ጥቅምና ፍላጎት በሚጎዳ መልኩ ወጥቶ በምዕመናን ግፊት እንዲቆም ተደርጓል፡፡ በወቅቱ የሰ/ጉባዔ የምዕመናን ተወካዮች ጭምር ሳያውቁትና ሳያምኑበት በጥድፊያና በጫና የወጣ ነው፣
§  ለትምህርት ቤት ግንባታ የወጣው ጨረታ በውል አፈጻጸም ስህተት /ክኗን ለተጨማሪ ወጪና ጥራት ለጎደለው ስራ ምክንያት ሆኗል፣

o   የሙዳይምጽዋት ቆጠራ ያለምዕመናን ተወካዮች ታዛቢነት እየተካሄደ ነው፣
o   ኢምክንያታዊና ከህግ ውጪ የሆኑ ክፍያዎች እየተካሄዱ ነው፣
o   ህግን ያልተከተለ የግዢ ስርዓት እየተፈጸመ መሆኑ እየተሰማ ነው፣
o   የደብራችን አስተዳዳሪ መኪና መግዛታቸውን እያየን ሲሆን የአስተዳደር ሰራተኞች ከገቢያቸው በላይ የተጋነነ ሀብት እያፈሩ ነው፣

 5.       ጤናማ አስተዳደራዊ ስርዓት መዘርጋት አልተቻለም፣
የተቋሟን አቅም እና መደበኛውን ሂደት ያልተከተሉ የሰው ኃይል ምደባ፣ ቅጥሮችና ዝውውሮች በስፋት እየታዩ ነው፡፡
ሰበካ ጉባዔው የማያውቃቸው ቅጥሮች በተለያየ ስም ይፈጸማሉ፤ የሀሰት ደብዳቤዎች እየተፈረሙ ይወጣሉ፤ የተለያዩ ንብረቶችና ሙዳየ ምጽዋት በየጊዜው እየጠፉ ነው፤ መንፈሳዊ አገልግሎት ቀርቶ የመደበኛ ቅጥር ተግባራት እንኳ እየተፈጸሙ አይደለም፡፡ ለምሳሌ የአስተዳደር ሰራተኞች በሰዓቱ በቢሯቸው አይገኙም፣ መደበኛ የአስተዳደር ጉባዔ አይካሄድም፤ አስተዳዳሪው በተዘጋጀላቸው ማረፊያ ውስጥ ሆነው የማይገኙባቸው የአበይት በዓላት ማህሌቶች፣ የእሁድ ሰንበት ቅዳሴዎች ብዙ ናቸው፡፡ በእለተ እሁድ በሰንበቴ ቤት በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት ጠፍቶ እንኳ ከማረፊያ ቤታቸው ተጠርተው መውጣት የማይችሉበት፣ ጉዳዩን ከማስተካከል ይልቅ በጓሮ በር የሚጠፉበት ሁኔታ ሁሉ ነበር፡፡ በዕለተ ሰንበት አስተዳዳሪው አውደምህረት ላይጉባዔ ሄደዋልተብሎላቸው በማረፊያቸው የሚታዩበት ጊዜ ተደጋጋሚ ነው፣

6.       የካቴድራሉ የይዞታ ደኅንነት አሳሳቢ ስጋት ውስጥ እንዲወድቅ ተደርጓል፣
o   የጥምቀተ ባህር ይዞታው ባለቤት አጥቶ ሌሎች እያጠሩት፣ የተረፈውንም ቦታ ጎርፍ እየሸረሸረውና ግለሰቦች ቆሻሻና አዛባ መድፊያ አድርገውት ይገኛል፤
o   በሊዝ የተገኙ ይዞታዎች (የት/ቤቱ፣ የክሊኒኩ …) ባለቤት አጥተው ምዕመኑን ከመንግስት ጋር የሚያጋጩበት አጣብቂኝ ደረጃ ላይ እንዲደርሱ ተደርጓል፣
o   በባዶ መሬት ላይ ኪራይ ተፈጽሞ በመንግስት ትዕዛዝ የተቋረጡ ውሎች ሳይቀር በድጋሚ ለተመሳሳይ ዓላማ እንዲከራዩ በማድረግ ይዞታውን የማስወሰድ የሚመስል ጥረት እየተደረገ ነው፣
እነኚህ ችግሮች በአጥቢያው ምዕመናን መንፈሳዊ ህይወትና በካቴድራሉ ደኅንነት ላይ የሚከተሉት መሰረታዊ ተጽእኖዎችን አምጥተዋል፣
·         በምዕመናኑ ውስጥ የነበረው አንድነት ተናግቷል፣
·         በደብሯ የነበረው የስብከተ ወንጌል ተስፋ አሽቆልቁሏል፣
·         ከይዞታዋ አንጻር የሚጠበቀው የልማት ርብርብ ቆሟል፣
·         ምዕመኑ አስተዳደሩ ላይ ያለው ዕምነት ጠፍቷል፣ ከቤ/ክኗም ርቋል፣ ገንዘብ የመስጠት ፍላጎቱም ቀንሷል፣
·         በሊዝ የተገኙ የደብሯ ይዞታዎች አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሰዋል፣
·         ምዕመናንና የወጣት ማህበራት የሚሰሩበት ምቹ ሁኔታና ተነሳሽነት እየሞተ ነው፣
  
. ለአሁኑ ዳግም ቅሬታችን ዋና ምክንያት የሆነው ጉዳይ
በብዙ መንገድ ህገወጥ የነበረ የስዕል ጨረታ አውጥተው ምዕመኑ ባደረገው ትግል እንዲሰረዝ ተደርጓል፡፡ ምክንያቱም  30 ቀናት ለተወዳዳሪዎች ክፍት እንዲሆን ህግ እያስገደደ 10 ቀን ብቻ የስዕል ጨረታው እንዲቆይ መደረጉ  በቀናነት የተፈጸመ የቁጥር ስህተት ብቻ አልነበረም፡፡ በሚሊዮን ብር የሚገመት ዋጋ ያላቸው የእነኚህ ቅዱሳን ስዕላት የጨረታ መወዳደሪያ ስፔስፊኬሽን ፈጽሞ 10 ቀን ሊዘጋጅ አይችልም፡፡ ምንአልባት በተለምዷዊ አካሄድ ከታየ መረጃው ተሰጥቶት ቀድሞ የተዘጋጀ ሰው ብቻ እንዲወዳደርበት በልክ የተሰፋ ጊዜ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በእናታችን ህንጻ ታሪካዊ ስዕላት ትውፊት፣ ትርጉምና ጥራት ላይ መደራደር መኖሩን የሚያሳይ ፍንጭ ነበር፡፡ በሀገሪቷ የጨረታ ህግም ወንጀል ጭምር ነበር፡፡   ለዚህም ምዕመኑ ተቆጥቶ፣ የሰበካ ጉባዔ የምዕመናን ተወካዮችም ሳናውቀው የወጣ ነው በማለታቸውና እነሱም ትተነዋል ብለው ቆሞ ነበር፡፡ ምክንያቱም

·         ያለሰበካ ጉባዔ የጋራ ስምምነት የወጣ ጨረታ ነበር፣
·         የስዕል ዕውቀት ያላቸው ባለሙያዎች ሳደራጁ፣ ቴክኒክ ኮሚቴ ሳይቋቋም የወጣ ጨረታ ነበር፣
·         ስራው የሚመለከተው የልማት ኮሚቴ ሳያውቅ የወጣ ጨረታ ነው፣
·         የሚሊዮን ብር ዋጋ ያለው ጨረታ ጋዜጣ ላይ እንዲቆይ የተደረገው  6 የስራ ቀናት ነው፣
·         ይህን ያህል ገንዘብ የሚጠይቅና ከአሸናፊው ጋር በጊዜ ገደብ ውል የሚገባበት ስራ ጨረታ የወጣው ስራውን ማስጀመሪያ የተወሰነ ገንዘብ እንኳ ሳይያዝ በጨበጣ ነው፣
·         የስዕል ጨረታ የወጣው ስዕሉ የሚሳልበት ህንጻ ርክክብ ሳይደረግ ነው፣
·         የስዕል ስራ ጨረታ የወጣው በቅደም ተከተል ሲቀመጡ አጣዳፊ የሆኑ ሌሎች ስራዎች ወደጎን ተደርገው ነው፣
·         የተጀመረው የጨረታ ሂደት እንዲቆም ሲደረግም ተድበስብሶ ነው፤ ለምዕመኑም ሆነ ጥያቄ ላቀረቡ አካላት በግልጽ የተባለ ነገር የለም፣
 ይህ ጨረታ አሁን በድጋሚ ጋዜጣ ላይ ወጥቷል፡፡ የወጣው 20 ቀን ብቻ ነው፡፡
·         የመጀመሪያው ጨረታ ከቆመ ከዓመት በላይ ዘግይቶ አሁን የወጣበት ምክንያት አጠራጣሪ ነው፣ ምክንያቱም
·         የዛሬ ዓመት ተገቢ አይደለም የተባለባቸው ሁኔታዎች በአብዛኛው አልተቀየሩም፣
·         ሰበካ ጉባዬው በተግባር ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ፈርሷል፤ የሶስት ዓመት ጊዜው ደግሞ አሁን ተጠናቋል፣

·        የካህናት ስብስብ ብቻ የሆነውና ከሱም የተጓደለው ሰበካ ጉባዔ እንኳ ጊዜውን በጨረሰበት፣ ምንም የተለየ ቅድመ ዝግጅት ሳይደረግ፣ አሁንም ለዚህ ስራ እጅግ አጭር በሆነ 20 ቀናት፣ እሱም የተመልካች ትኩረት እንዳይስብ ሆን ተብሎ ርዕሱ ግልጽነት እንዲጎድለውየጨረታ ማስታወቂያተብሎ፣ ያምልማት ኮሚቴየተባለው እንኳ ሳያውቀው፣ በገንዘብም በሀሳብም አንድም ቅድመ ዝግጅት ሳይደረግ በዚህ መልኩ መውጣቱ በምንም ምክንያት ለቤ/ክኗ እና ለምዕመኖቿ ጥቅም ነው ብሎ አያሳምንም፡፡
አባቶቻችንን የምንለምነው ነገር የሚከተሉትን ነው፣
·         ሀገረ ስብከቱ የደብራችንን ችግር በጥልቀት የሚያውቀው በመሆኑና ቆይታቸውም ከበቂ በላይ ስለሆነ በጽ/ቤት ያሉ የአስተዳደር ሰራተኞችን  እንዲያነሳልን፣
·         ለካቴድራላችን የሰላም፣ የልማትና የስብከተወንጌል ጥያቄ የሚመጥኑ አባቶች በምትካቸው እንዲመድብልን፣
·         ለቀጣይ አሰራር ጠቃሚ አቅጣጫ ማስቀመጥ እንዲቻል በደብራችን ውስጥ የነበሩ የፋይናንስና የአስተዳደር አሰራሮች በውጭ ኦዲተር እንዲፈተሽ  እንዲፈቀድልን፣
·         የስዕል ጨረታውን ጨምሮ ከፍተኛ የገንዘብ ዝውውር የሚጠይቁ ስራዎች ህጋዊነት ተመርምሮ ውሳኔ እስኪሰጠው ድረስ ለጊዜው እንዲቆምልን፣
·         አጠቃላይ የምዕመናን ጠቅላላ ጉባዔ ተጠርቶ ለቀጣይ ስራ ዕምነትና ሰላም የሚያወርድ ውይይት እንዲደረግና ጠንካራ ሰበካ ጉባዓ እንዲመረጥ እንዲያደርግልን ስንል በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን፣
 ከመንፈሳዊ  ሰላምታ ጋር

No comments:

Post a Comment